የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት መረጃ አስተዳደር ስርዓት (CoPIMS) ትግበራ ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት መረጃ አስተዳደር ስርዓት (CoPIMS) ትግበራ ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የጥምር ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት መረጃ አስተዳደር ሥርዓት (COPIMS) ልማት እና ትግበራ የCOPIMS ሥርዓት ሥልጠና እየሰጠ ነው ።
አዲስ አበባ ጥቅምት 24/2/2019 ዓም (ው.ኢ.ሚ)
የCWA2 ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ታደለ ገዛኸኝ ሥልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት ሲሆን፤ ሲስተሙ የወረቀት ሥራን በመቀነስ፣ መጓተትን በማስወገድ እና ተጠያቂነትን በማጠናከር በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ለመስጠት ያለውን ቁልፍ ሚና ገልጸዋል።
የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (BiT) የጥምር ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት መረጃ አስተዳደር ሥርዓት (COPIMS) ልማት እና ትግበራ ስምምነት በሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. የተፈረመ መሆኑን አውስተው ፕሮግራሙ በአምስት የፓይለት CR-WASH የውኃ አቅርቦት ፕሮጀክቶች (ኤልዋያ፣ ጉራዳሞሌ፣ ያያ-ወርቄ፣ ታንቋ-አበርገሌ እና ዛላ) ተለይተው መረጃዎቻቸው ወደ ሥርዓቱ መግባታቸውን አቶ ታደለ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ሲስተሙን ላበለጸገው እና ስልጠናውን እየሰጠ ላለው የባህር ዳር ዩንቨርስቲ ምስጋና በማቅረብ ከአሁን ቡሀላ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር በሚደረጉ የፕሮጀክቶች መረጃ ልውውጥ እና የሪፖርት አቀራረብ ሂደቶች በሲስተሙ በኩል ብቻ እንዲጠቀሙ አሳስበዋል ።
በሥልጠናው ላይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቴክኒክ ሠራተኞች እንዲሁም በፕሮጀክቶቹ የሚሳተፉ ኮንትራክተሮችና አማካሪዎች ስለ ሲስተሙ የመጀመሪያ ደረጃ ገለጻና አጠቃላይ ሥልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል።
ስልጠናው በነገው እለትም እንደሚቀጥል አስተባባሪዎች ገልጸዋል፡፡