በ3ኛው የውኃና ኢነርጂ ሳምንት ማጠቃለያ የቀድሞ ሚኒስትሮች ተሞክሯቸውንና አመራራቸውን አብራሩ።
በ3ኛው የውኃና ኢነርጂ ሳምንት ማጠቃለያ የቀድሞ ሚኒስትሮች ተሞክሯቸውንና አመራራቸውን አብራሩ።
ጥቅምት 20/2019ዓም (ው.ኢ.ሚ)
አምስተኛ ቀኑን ባስቆጠረው የውኃና ኢነርጂ ሳምንት የመዝጊያ መድረክ ላይ የተገኙ አምስት የዘርፉ የቀድሞ ሚኒስትሮች ተቋሙ በየዘመናቱ «ከየት ወደ የት» እንደመጣ የሚያሳይ ስፊ ልምድና ሙያዊ ትንታኔ አቅርበዋል።
በመድረኩ ላይ የቀድሞ ሚኒስትሮቹ የፖሊሲና እስትራቴጂ ቀረጻ ተቋሙን ከስረ-መሰረቱ ለመገንባት፣ የሕግና ፖሊሲ ማዕቀፎችን ለማዘጋጀት እንዲሁም መመሪያዎችን ወደ ተግባር ለመለወጥ የተከናወኑ አቅኚ ስራዎችን አብራርተዋል።
ሀገራዊና አህጉራዊ እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ ኢትዮጵያ በውኃ ሀብት አጠቃቀምና በታዳሽ ኢነርጂ ልማት ዙሪያ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተገበሩትን እና በድንበር ተሻጋሪና አህጉራዊ መድረኮች ያሳዩትን ጠንካራ የዲፕሎማሲና የቴክኒክ አመራር ገልጸዋል።
የመጠጥ ውኃና ኢነርጂ ተስፋፊነት ለዜጎች ንጹሕ የመጠጥ ውኃ ለማቅረብ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ተዳራሽነትን ለማስፋፋት እና ታላላቅ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ለመምራት የተሄዱባቸውን ረጅም መንገዶች አውስተዋል።
የውኃ አካላት እንክብካቤና ዘላቂነት የተፈጥሮ ሀብት አያያዝ፣ የውኃ አካላት ጥበቃ እና የካችመንት ማኔጅመንት ስራዎች ዘላቂ ጠቀሜታቸውን አጉልተው አሳይተዋል።
በመጨረሻም ተግዳሮቶችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች በየዘመናቸው ያጋጠሟቸውን የፋይናንስ፣ የቴክኖሎጂ፣ የሰው ኃይል እና የፖሊሲ ማነቆዎች በመዳሰስ፣ ለወደፊቱ የዘርፉ እድገት የሚረዱ ስትራቴጂካዊ የመፍትሔ ሃሳቦችንና አቅጣጫዎችን ጠቁመዋል።