በኢትዮጵያ የውሃ ደህንነትን ለማረጋገጥ የውሃ ሀብትን በተቀናጀ፣ በሳይንሳዊ እና በዘላቂነት መርህ ማስተዳደር እንደሚያስፈልግ ተገለፀ
በኢትዮጵያ የውሃ ደህንነትን ለማረጋገጥ የውሃ ሀብትን በተቀናጀ፣ በሳይንሳዊ እና በዘላቂነት መርህ ማስተዳደር እንደሚያስፈልግ ተገለፀ
ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) ለውሃና ኢነርጂ ዋስትና የተጠበቀለት የወደፊት ሁኔታ ሳይንሳዊ መሠረት ያላቸውን ፖሊሲዎችና አጋርነቶችን ማሳደግ ''በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀው 3ኛው የኢትዮጵያ የውሃና ኢነርጂ ሳምንት ማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ በኢትዮጵያ የውሃ ደህንነትን ለማረጋገጥ የውሃ ሀብትን በተቀናጀ፣ በሳይንሳዊ እና በዘላቂነት መርህ ማስተዳደር እንደሚያስፈልግ ተገለፀ።
በሳምንቱ ቆይታ በሳይንስና ፈጠራ፣ በአረንጓዴ ኢነርጂ ሽግግር፣ በውሃ ዲፕሎማሲና በተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ዙሪያ ውይይቶች የተካሄዱ ሲሆን የውሃና የኢነርጂ ትስስርም በፖሊሲ ደረጃ ብቻ ሳይወሰን ወደ ተግባር ማሸጋገር እንደሚገባ ተጠቁሟል።
በተጨማሪም የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር በተግባር እንዲሳካ የተፋሰስ ዕቅድን ማጠናከር፣ የውሃ መረጃ ስርዓትን ማሳደግ፣ የውሃ ሀብት መገኛና አጠቃቀምን በትክክል መለየት እንዲሁም የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑ ተጠቅሷል።
የውሃና ኢነርጂ ደህንነትን ለማረጋገጥ በሳይንስ ላይ የተመሠረተ፣ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓቶችን ተግባራዊ በማድረግ እና በሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ የሚመራ አስተዳደር መከተል እንደሚገባም በውይይቱ ላይ ተነስቷል።