በኤል ኒኖ ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን አደጋ ለመግታትበ የሜትሮዎሎጂ ትንበያዎች መከታተል ይገባል።

በኤል ኒኖ ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን አደጋ ለመግታትበ የሜትሮዎሎጂ ትንበያዎች መከታተል ይገባል። ​መስከረም 17/2019 ዓ.ም (ውኢሚ) የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት በያዝነው የክረምት ወቅት በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች ከመደበኛ በታች የሆነ ዝናብ እንደሚኖር በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ ከፍተኛ ዝናብ በመጣሉ ምክንያት የጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ባደረገው ትንበያ መነሻነት የውኃና ኢነርጂ ዘርፉን ያካተተ ስራዎችን እያከናወነ ነው። ​የኤል ኒኖ (El Nino) ተፅዕኖ በውኃ ሀብትና በኃይል አቅርቦት ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቋቋም ​የውኃ ሀብት አጠቃቀምና ጥበቃ ላይ ከመደበኛ በታች ዝናብ በሚያገኙ እና ለድርቅ በሚጋለጡ አካባቢዎች የውኃ እጥረት እንዳይከሰት የከርሰ-ምድርና የገፀ-ምድር ውኃ ሀብቶችን በአግባቡ የማቀብ፣ ሥራዎች እየተሠሩ ነው። ​የግድቦችና የኃይል ማመንጫዎች ደህንነት ከፍተኛ ዝናብ በሚጥልባቸው አካባቢዎች የጎርፍ አደጋ በኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች፣ በግድቦችና በውኃ መሠረተ-ልማቶች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ቅድመ-ማስጠንቀቂያዎችን በመጠቀም ሥራዎችም እየተሰሩ ነው። ​የአስቸኳይ ጊዜ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት በውኃ እጥረት ለሚመቱ አካባቢዎች የጣሪያ ላይ ውሃ የማሰባሰብ ስራዎችንም ተግባራዊ አድርጓል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ​የተፋሰስና የጎርፍ ስጋት አመራር የጎርፍ ስጋት በሚታይባቸው ተፋሰሶች አካባቢ የሚገኙ የውኃ መሠረተ-ልማቶችን ከተፈጥሮ አደጋ የመጠበቅና የጎርፍ አቅጣጫ የማስቀየስ ተግባራት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እየተከናወኑ ይገኛሉ። በመጨረሻም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ቷቋም በኩል የሚሰጣቸውን ትንበያዎች በመጠቀም እና መነሻ በማድረግ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ የህብረተሰቡን ከጉዳት ለመጠበቅ የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል። ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ፌስቡክ https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/ ቴሌግራም http://t.me/mowieethiopia ዌብሳይት http://mowe.gov.et X/ትዊተር https://x.com/mowe_ethiopia ዩቱዩብ https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s ቲክቶክ tiktok.com/@mowetikt

Share this Post