በኩልፎ ወንዝ የተሰሩ እና ለሚሰሩ የጎርፍ መከላከል ስራዎች የመስክ ምልከታ ተካሄደ።
አርባ ምንጭ መስከረም12/2019 ዓ.ም
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት በአርባ ምንጭ ኩልፎ ወንዝ አካባቢ ለሚከናወኑ የጎርፍ መከላከል ስራዎች የመስክ ምልከታ እና የቴክኒክ ግምገማ አካሄደ።
በአቶ ሱራባ ዳኒ የተመራው የዓለም ባንክ ልዑካን ቡድን እና የኢትዮጲያ ጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት ቡድን ባለፈው ባካባቢው ያስከተለውን የጎርፍ አደጋ መነሻ በማድረግ በኩለፎ ወንዝ ላይ ጥሎት የሄደውን የደለል ክምችት ለማንሳት እና በተገቢው ቦታ ለማስወገድ የተሰራውን ስራ እንዲሁም በበጀት ዓመቱ ትኩረት በሚሹ አደጋ ተጋላጭ ቦታዎች ላይ የተሰራው የዲዛይን ስራ ወደ ትግበራ ለማስገባት በቦታው ተገኝተው የመስክ ምልከታ ያደረጉ ሲሆን፣ የዓለም ባንክ ብድን የወንዝ ደለል የማስወገድ የስራ ሂደት እና አሁናዊ የወንዙ ይዞታ እንዲሁም በስራዎቹ ላይ የማህበራዊና አካባቢ ጥበቃ ተጽእኖዎች ላይ ጠቃሚ ግብአቶችን አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት በበጀት ዓመቱ የሚሰሩ የጎርፍ መከላከል ስራዎች በተመለከተ በተለይ የኩልፎ ወንዝ የጎርፍ ስጋት ሊቀንሱ የሚችሉ ዋናው የዲዛይን ስራዎች አልቀው ወደ ግንባታ ለመግባት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን እና ከዚህ በፊት በአካባቢው የነበረውን የጎርፍ ችግር መነሻ በማድረግ ለቡድኑ በፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ተመስገን ከተማ ገለፃ ተደርጓል፡፡
በዚህ የምልከታ መርሃ-ግብር ላይ ከአርባ ምንጭ ከተማ መዘጋጃ ስራስኪያጅ አቶ ገዳሙ እንደገለፁት የጎርፍ ክስተቱን በዘላቂነት ለመፍታት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው፤ ለመስራት የታሰበው የመከላከል ስራ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ወደ ትግበራ እንዲገባና ማንኛውንም ድጋፍ እንደሚያደርጉም ጠቁመዋል፡፡
በመጨረሻም ማጠቃለያ ውይይት ተደርጎ የመስክ ምልከታው ተጠናቋል።
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto