የከርሰ ምድር ውሃ ቁፋሮና ግንባታዎችን በጥራት ለማከናወን የሚያችል የአቅም ግንባታ ሥራ ተከናወነ
ሀዋሳ፣ መስከረም 12/2019 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የከርሰ ምድር ውሃ ጥናት፣ ቁፋሮና ግንባታዎችን በተሻለ ጥራትና ደረጃ ለማከናወን ሰፊ የአቅም ግንባታ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ።
ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እንዲሁም ከክልሎች የውኃና ኢነርጂ ቢሮዎች የተውጣጡ 20 የከርሰ ምድር ውሃ ጥናትና ቁፋሮ ባለሙያዎችን ያሳተፈ የሙያተኞች የአቅም ግንባታ ሥልጠና በሀዋሳ ከተማ ተሰጥቷል።
ለስድስት ቀናት በንድፈ ሀሳብና በተግባር ተደግፎ የተሰጠው የዚህ ሥልጠና ዓላማ በኢትዮጵያ የከርሰ ምድር ውሃ ጥናትና ቁፋሮ ሥራዎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ፣ በተሻለ ጥራትና ደረጃ ለማከናወን የባለሙያዎችን አቅም ማጎልበት ነው።
የክቡር የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ እና የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ አበራ እንደሻው እንደገለጹት፤ ሚኒስቴሩ
የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መቀመጫውን እንግሊዝ ለንደን ካደረገ Children’s Investment Fund Foundation (CIFF) ከተባለው የልማት አጋር ድርጅት ጋር የዘርፍ ትብብር ስምምነት አድርጓል።
በዚሁ መሠረት በከርሰ ምድር ውሃ ጥናትና ቁፋሮ ዘርፍ የአቅም ግንባታ ሥራዎች መስራት መጀመሩን አስታውሰው፤ ከአጋር ድርጅቱ ጋር የረጅም ጊዜ ስምምነት መሠረት የከርሰ ምድር ውሃ ጥናት፣ ቁፋሮና ግንባታ ሥራዎችን በተሻለ ጥራትና ደረጃ ለማከናወን ሰፊ የአቅም ግንባታ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።
የከርሰ ምድር ውሃ ጥናትን በዘመናዊ ዘዴ ለማከናወን የሚያስችሉ ዘመናዊ መሣሪያዎች በ500 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ከውጭ ተገዝተው ወደ ሀገር እየገቡ መሆኑን ጠቁመዋል።
ለጋሽ ድርጅቱ በጥናት ድጋፍ ብቻ ሳይወሰን እስከ 15 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በመመደብ የጥልቅ ከርሰ ምድር ውሃ መቆፈሪያ ማሽኖችን፣ ከባድና ቀላል ተሸከርካሪዎችን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ መሣሪያዎችን ግዥ በመፈጸም ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አቶ አበራ ገልጸዋል።
ሥልጠናውን የሰጡት ከዴንማርክ የመጡ የዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች ሲሆኑ፣ የአቅም ግንባታ ሥልጠናው የሚኒስቴሩን ጥያቄ ተከትሎ በለጋሽ ድርጅቱና በመሣሪያ አምራች ድርጅቱ መካከል በተደረገ የግዥና የአቅም ግንባታ ስምምነት መሠረት መሆኑ ተገልጿል።
የሥልጠናው ተሳታፊዎች የከርሰ ምድር የመጠጥ ውሃ ጥናትና ቁፋሮ ሥራዎችን ለማከናወን ቀደም ሲል ይጠይቅ የነበረውን ጊዜና ድካም በእጅጉ ለመቀነስ የሚያስችል ስልጠና ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
እንዲሁም የከርሰ ምድር ውሃ ሀብትን በተሻለ መንገድ ለመለየት፣ ለመጠቀምና ለማልማት እንዲሁም የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለማሻሻል ጉልህ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው ጠቅሰዋል። ለተቋማችን ተጨማሪ መረጃ ለማገኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetik