አስተማማኝ የሚቲዎሮሎጂ መረጃን ወደ ተግባር መቀየር ሕይወትን ይታደጋል፤ ሀብትንም ይጠብቃል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አስተማማኝ የሚቲዎሮሎጂ መረጃን ወደ ተግባር መቀየር ሕይወትን ይታደጋል፤ ሀብትንም ይጠብቃል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ው.ኢ.ሚ)፦ አስተማማኝ የሚቲዎሮሎጂ መረጃን ወደ ተግባር መቀየር ሕይወትን ይታደጋል፤ ሀብትንም ይጠብቃል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል። ተቋሙ የተሟላ የአየር ትንበያ አገልግሎት በመስጠት ለሀገሪቱ ልማትና አቅም ወሳኝ ሥራዎችን የሚያከናውን የረጅም ዘመን እድሜ ያለው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ላይ አስፍረዋል። ‎ ጉብኝቱ እየተለዋወጠ ያለውን የአየር ፀባይና የአየር ንብረት ሁኔታዎችን በትክክል ለመረዳት እንዲሁም ምላሽ የመስጠት አቅምን ለማጠናከር፤ የሚቲዎሮሎጂያዊ መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የሳይንሳዊ ምርምር እና የቴክኖሎጂ ዕድገት ያለውን የላቀ ጠቀሜታ የሚያረጋግጥ መሆኑን አመልክተዋል። ‎ ‎እንደ ኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ያሉ ተቋማትን ማጠናከር እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል። ግብርና፣ ውሃ፣ ጤና፣ አቪዬሽን እና የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራርን ጨምሮ ቁልፍ ዘርፎች የሚደገፉባቸውን አገልግሎቶች ለማሻሻል በሰው ኃይል አቅም ግንባታ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እና በመረጃ መሠረተ-ልማት ላይ መዋዕለ-ንዋይ ማፍሰስ ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመተንበይ፣ የትኞቹ አካባቢዎች ላይ ጣልቃ ገብነት ይበልጥ እንደሚያስፈልግ ለመወሰን፣ እንዲሁም ወቅታዊና ውጤታማ በሆነ መንገድ እንድንቀሳቀስ ለማድረግ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶች ያላቸው ጠቀሜታ አበረታቶኛል ሲሉ ገልጸዋል። አስተማማኝ መረጃ ወደ ተግባራዊ መመሪያዎች ሲቀየር ሕይወትን ይታደጋል፣ ሐብትን ይጠብቃል፣ እንዲሁም የተሻለ ውሳኔ ለመስጠት እንደሚያግዝም ነው ያነሱት። የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎቱ ከሳተላይት ምልከታ ባለፈ ሰፊ መዋቅር ያለው መሆኑን ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መረጃዎችን በወቅቱ ሰብስቦ፣ አቀናጅቶና ተንትኖ ፈጣን እርምጃ ለመውሰድ በመላ ሀገሪቱ የተዘረጉ ጠንካራ የመረጃ መሰብሰቢያ ጣቢያዎችና የማዕከላት መረብ ወሳኝ መሠረት መሆናቸውን ገልጸዋል። ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ፌስቡክ https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/ ቴሌግራም http://t.me/mowieethiopia ዌብሳይት http://mowe.gov.et X/ትዊተር https://x.com/mowe_ethiopia ዩቱዩብ https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s ቲክቶክ tiktok.com/@mowetikto

Share this Post