Jun 2026

የኢትዮጵያ የከርሰ ምድር ውሃ ጥናት እና የውሃ ጉዶጓድ ቁፋሮና ግንባታ መመሪያዎች ለባለድርሻ አካላት ቀርበው ግምገማ ተካሄደባቸው።

ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ አስቀድመው በከርሰ ምድር የውሃ ሃብት ዘርፍ በስራ ላይ የቆዩ፣ሲሰሩ የነበሩና አሁንም ስራውን በመምራት ላይ የሚገኙት ሙያተኞች እስከአሁን ላበረከቱት አስተዋፅኦ አመስግነው ይህ ተግባርም አበረታች ውጤት እያስመዘገበ ያለ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ በአጽንኦት አሳስበዋል።

ብሔራዊ የኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም (NEP 3.0) ፍኖተ ካርታ ላይ ውይይት ተካሄደ።

የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ የብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም (NEP 3.0) እ.ኤ.አ በ2035 ሁለንተናዊ አስተማማኝ፣ ተመጣጣኝ እና ዘላቂ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነትን ለማስፈን የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ግብ ነው ብለዋል።

የብቃት ምዘናው የሪፎርሙን ስኬት የሚያረጋግጥ ወሳኝ መሳሪያ ነው። ዶ/ር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ፣ የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ ሰራተኞች ጠንካሮችና ብቁ በመሆናቸው የብቃት ምዘናውን በውጤታማነት እንደሚያጠናቅቁ ያላቸውን እምነት በመግለጽ ሰራተኞቹን አበረታተዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ እየተሰራ ነው - ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ እየተሰራ መሆኑን በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ገለጹ።

ውሃ ለሀይድሮ ፓወር፣ ለመስኖና ለመጠጥ ብቻ ሳይሆን ለሴቶችና ለልጃገረዶች በወር አበባቸው ወቅት ንፅህናቸውን በአግባቡ ለመጠበቅ የማይተካ ሚና አለው ተባለ።

የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት አቶ ተስፋዬ ፊቻላ ሴቶችና ልጃገረዶች የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ ማግኘት ከፍተኛ ተግዳሮት የሆነባቸው በርካታ ሴቶች በገጠርም ሆነ በከተማ የሚገኙ ሲሆን የወር አበባቸውን ምቹ በሆነ ሁኔታ ማስተናገድ ካለመቻል የተነሳ ሴት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ቀሪ ማብዛት

በHuman Capital Project (HCP) አዘጋጅነት የባለድርሻ አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠና መድረክ ተካሄደ።

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የHuman Capital Operation ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ ዱጉማ በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ እንደገለጹት ፕሮጀክቱ በቁጥር መቶ በሚደርሱ የዓለም ሃገራት የሚተገበር መሆኑን አስረድተዋል።

በግንባታ ላይ የሚገኙ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የቅርብ ክትትል እየተደረገ ነው - ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ

ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ፣ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ በዓለም ባንክ ድጋፍ እየተገነባ የሚገኘውን የንፁህ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክትን

የተለያዩ ተቋማት ለሚሰጧቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈሉ የአገልግሎት ክፍያዎችን ለመወሰን የቀረበው ረቂቅ ደንብ ወደ ስራ እንዲገባ ተወሰነ

ምክር ቤቱ ተወያይቶ ውሳኔ ካሳለፈባቸው 5 ጉዳዮች መካከል የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ተቋማት ለሚሰጧቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈሉ የአገልግሎት ክፍያዎችን ለመወሰን የቀረበው ረቂቅ ደንብ ይገኝበታል።

በኢትዮጵያ የውሃ ዋጋ ትመና እና ዘላቂ አካታች እድገት ላይ ያተኮረ የውይይት ተካሄደ።

በሚኒስትር ዲኤታ ማእረግ የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳ እንደገለጹት የውሃ ሃብት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ መሰረት፣ የምግብ ዋስትና ምሰሶ እና የማህበራዊ እኩልነት መገለጫ በመሆኑ፣ ሃብቱን በአግባቡ መገምገምና ማስተዳደር ለሀገሪቱ የወደፊት ህልውና ወሳኝ ነው ብለዋል። ​

የመንግስት አገልግሎት ሪፎርሙን ለማሳካት የብቃትና ምዘና ማዕቀፍ ስልጠና ለውሃና ኢነርጂ ዘርፍ አመራሮችና ሠራተኞች ተሰጠ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚና የዘርፉ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የአብይ ኮሚቴ ጸሀፊ አቶ ኦልቀባ ባሼ ሲሆኑ፣ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በሁለተኛው ዙር የሪፎርም ትግበራ ውስጥ ከተካተቱ ተቋማት አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።

የአፍሪካ ቻይልድ ሚኒ ግሪድ ፕሮጀክት በሚኒ-ግሪድ ታሪፍ ማስያ መተግበሪያ ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ነው።

በዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በዩኤን ዲፒ የአፍሪካ ቻይልድ ሚኒ ግሪድ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ይመስላል ተፈራ ስልጠናው በዘርፉ ያሉ የቁጥጥር ማዕቀፎችን፣ ምርጥ ተሞክሮዎች እና የታሪፍ አወሳሰን ስልቶችን ያካተተ ሲሆን ተሳታፊዎች የቴክኒክና የፋይናንስ መረጃዎችን ወደ ስራ በመቀየር ረገድ ያላቸውን እውቀት ያሳድጋል ብለዋ

ተፈትኖ ያለፈው የባስኬት ፈንድ ፕሮግራም

ፕሮግራሙ የተቀረጸው የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን በከተሞች የማሳደግ ዓላማ በመያዝ ሲሆን፤ በተበታተነ መንገድ የሚገኘውን የፋይናንስ ድጋፍ በአንድ ቋት በማሰባሰብ በተደራጀ መልኩ ትርጉም ያለው ስራ ለመስራት ነው።

የመጠጥ ውሃ ተቋማት በዘላቂነት አገልግሎት እንዲሰጡ ህብረተሰቡ እንደግል ንብረቱ ሊንከባከብ ይገባል ተባለ።

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ልማት ፈንድ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ዶጊሶ ጎና የውሃ ልማት ፈንድ ከተቋቋመ 23 ዓመታት ቢሆነውም በረጅም ጊዜ ብድርና በአነስተኛ ወለድ የተገኘ ሀብትን በማስተባበር በውሃ ልማት ዘርፍ በርካታ ስራዎች ሲሰሩ እንደነበር አስታውቀዋል።

ከ227 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የፀሓይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ ዛሬ ያሰመረቅነው ፕሮጀክት ከ227 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት እና ከ2 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን የኤሌክትሪክ ሀይል ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት ጋር የባዮጋዝ ማብላያ ፕሮጀክት ወቅታዊ ሁኔታና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አካሂዷል።

ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ ከዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ጋር ፕላንቱ መጀመሪያ ሲገነባ የምርምር ማዕከል እንዲሆን ታሳቢ የተደረገና ከኃይል አቅርቦት ባለፈ ዋነኛ ዓላማው የተፈጥሮ አፈር ማዳበሪያውን በመጠቀም ገቢ መፍጠርና ግብርናን ምርት በማሳደግ የምግብ ሉአላዊነትን ማረጋገጥ ላይ ያተኮረ ነው ብለዋል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የከርሰ ምድር የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ለማካሄድ የውል ስምምነት ተፈራረመ።

በሚኒስቴር ዴኤታ ማዕረግ የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳ ሲሆኑ የውል ስምምነቱ የተፈረመው ከሚድሮክ ጂኦ ኤክስፕሎሬሽን ኃላ.የተ.የግ.ኩባንያ (ደቡብ ኢትዮጵያ አባያ -ጫሞ ሳይት)፣ ከአልባዴ ጠቅላላ ኮንስትራክሽንና የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ኃላ.የተ.የግ.ኩባንያ (ደቡብ ምዕራብ ጊምቦ- ጬና ሳይት) እና ከ

የባስኬት ፈንድ ፕሮግራም 43 ከተሞችን ንፁህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ የማቺንግ ፈንድ ፕሮግራም እ.ኤ.አ በ2016 ስንጀምር የጋራ ራዕያችን ለማሳካት በፍጥነት በማደግ ላይ ለሚገኙ ትንንሽ እና መካከለኛ ከተሞችን ለማቋቋም ዘላቂ የውሃ እና የንፅህና አጠባበቅ ስርዓት ለመገንባት ያለመ ነበር ብለዋል።

በያንጉዲ ወረዳ የአፈርና ውሃ ጥበቃና የጎርፍ አደጋ መከላከል የልማት ሥራ ለማስጀመር የባለድርሻ አካላት የማኅበረሰብ ንቅናቄ መድረክ ተካሄደ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተፋሰስ ልማትና ጎርፍ መከላከል ዴስክ ኃላፊ አቶ በቀለ ብዙወርቅ የባዘርኔት ፕሮጀክት አንዱ ኮምፖነንት በሆነው የአፈርና ውሃ ጥበቃ እና የጎርፍ መከላከል ሥራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው፣ ፕሮጀክቱ በያንጉዲ ወረዳ የሚታዩ የአፈር መሸርሸር፣ የመሬት መራቆት እና የጎርፍ አደጋዎችን

የውሃ ሀብታችንን በዘላቂነት ለማስተዳደር፣ ለማረጋገጥ እና የዜጎችን የአገልግሎት ጥራት ለማሻሻል ደንበኛን ያማከለ አገልግሎት አሰጣጥን ማጠናከር አስፈላጊ ነው ተባለ።

በውይይት መድረክ ላይ የውሃ ሀብታችንን በዘላቂነት ለማስተዳደር፣ ለማረጋገጥ እና የዜጎችን የአገልግሎት ጥራት ለማሻሻል ደንበኛን ያማከለ አገልግሎት አሰጣጥን ማጠናከር አስፈላጊ ነው ያሉት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ተቋሙ ለከተማ መጠጥ

በቤዚን አቀፍ የዘላቂነት ማረጋገጫ/BaSRINET/ፕሮጀክት አማካኝነት በንግድና ስራ ፈጠራ ዙሪያ የተሰጠው ስልጠና የሴቶችን ተጠቃሚነት በሚገባ የሚያረጋግጥ ነው - ተሳታፊዎች

የዋቢሸበሌ ባዘርኔት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ኢሊያስ ሁሴን እንዳመለከቱት ፕሮጀክቱ በአካባቢው አቅዶ ከሚተገብራቸው ቁልፍ ተግባራት መካከል የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት የሚገጥሙ ማህበራዊ ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት ዋናው ስራ ሲሆን በስራ ፈጠራና ክህሎት ላይ ተመርኩዞ የተዘጋጀው ይህ መድረክ የሴቶችን የኑሮ ሁኔ

የኢነርጂ ዘርፍ የሚጨበጥ የተስፋ ጉዞ

ኢነርጂ የኢንዱስትሪ መስፋፋት፣ የግብርና ምርታማነት እና የአገልግሎት ዘርፍ ዕድገት ቁልፍ ግብዓት ነው። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት "የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ማዕከል" ለመሆን በምታደርገው ጥረት የኢነርጂ መሰረተ ልማት ዝርጋታ የሀገሪቱን የሁለገብ ዕድገት ለማፋጠን ወሳኝ ሚና ይጫወታል።

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት 100 ዘመናዊ የአየር ሁኔታ ጣቢያዎችን ለመትከል የግዥ ውል ፈረመ።

የኢንስቲትዩቱ የትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አሳምነው ተሾመ እንደገለጹት፣ ጣቢያዎቹ በጎርፍ መከላከል ፕሮጀክቱ በሚተገበርባቸው የአዋሽ፣ የስምጥ ሸለቆ ሐይቆች እና የኦሞ–ጊቤ ተፋሰሶች አካባቢዎች ላይ እንደሚተከሉ ገልጸዋል።

የከተማ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን አገልግሎት ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ለማቋቋም በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ውይይት ተደረገ።

ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ የከተሞች የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን አገልግሎት ተቆጣጣሪ ባለስልጣንን ለማቋቋም እየተሰራ ያለውን ሂደት ለማሳወቅ፣ የሚቋቋመው የፌዴራል ተቆጣጣሪ ባለስልጣን አዋጅ ላይ ማብራሪያ ለመስጠት እንዲሁም ባለስልጣኑ ሊጠቀምባቸው በሚችለው መሠረታዊ የቁጥጥር መሣሪያዎች ላይ ስልጠናና

የቤዚን አቀፍ የዘላቂነት ማረጋገጫ ፕሮጀክት ዋቢ ሸበሌ ተፋሰስ በንግድና ስራ ፈጠራ ዙሪያ ለሴቶች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ነው።

የሸበሌ ዞን ምክትል አስተዳደር አቶ ኢሴ አብዱላሂ በራኪ በበኩላቸው የቤዚን አቀፍ የዘላቂነት ማረጋገጫ ፕሮጀክት የተለያዩ የልማት ስራዎችን በዘላቂነት ለመፍታትና በዋቢ ሸበሌ ተፋሰስ የአካባቢውን የተፈጥሮ ሃብት የሚያጎለብቱና የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው የተዘጋጀውን የአቅም ማጎ

በ405 ሚሊዮን ዶላር የሚተገበረው የHCO ፕሮጀክት በ65 ወረዳዎች ውጤታማ ስራዎችን እያከናወነ ነው ተባለ።

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የHuman Capital Operation ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሀብተሙ ዱጉማ እንደገለጹት፣ ፕሮጀክቱ ከአዲስ አበባ በስተቀር በሁሉም ክልሎች በሚገኙ 65 ወረዳዎች ላይ እየተተገበረ ሲሆን፣ በተለይም የሰው ሀብት ልማት ዝቅተኛ በሆነባቸው፣ በድርቅ ተጽዕኖ በሚደርስባቸው፣ በድንበር አካባቢዎች

በአደሌ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና በልማት ባንክ በኩል እየተከናወኑ ያሉት የኤሌትሪፊኬሽን ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ተገመገመ፡፡

ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ በመጀመርያ የገመገሙት በአደሌ ፕሮጀክት በአዲስ አበባ እና በሌሎች የክልል ከተሞች ማለት አምቦ፣ ነቀምት፣ አሶሳ፣ ቢሾፍቱ፣ ሱልልታ እና ደብረብሃን እየተከናውነ ያሉት የኔትዎርክ ማሻሽያና ማጠናከርያ ስራዎችን እና በዝግጅት ምዕራፍ ባሉት ጂጅጋ፣ ሆሳእና፣ ዲላ እና አሰላ የገመገሙ ሲሆን

በHCO ፕሮጀክት በኢነርጂው ዘርፍ ለሚከናወኑ ተግባራት አጋዠ የሆነ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ሲሆኑ፣ HCO ፕሮጀክት በኢትዮጵያ እና በዓለም ባንክ ትብብር የሚተገበር የሰው ኃይል ልማት ፕሮግራም በመሆኑ የመሠረታዊ ማህበራዊ አገልግሎቶችን ጥራት፣ ተደራሽነት እና ቀጣይነት በማሻሻል በውሃ፣ በሳኒቴሽን፣ በጤና፣ በትምህርት እና በኢነርጂ ዘርፎች የሕዝብን ኑሮ ለማሻሻ

አገር በቀል ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም አማራጭ ሳይሆን አዋጭ ነው ተባለ።

አቶ ታምሩ ገደፋ የፍሎራይድ ችግርን ለመቅረፍ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ጥረቶች ሲደረግ መቆየቱን አስታውሰው፤ በስምጥ ሸለቆ አካባቢ በይበልጥ ችግሩ አሳሳቢና ቀስ በቀስ በጤና ላይ ችግር የሚያስከትል በመሆኑ ችግሩን ለማቃለልና ለመቀነስ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በአስር አመት ስትራቴጂ ዕቅድ ውስጥ በማካተት በጀት በመመደ

ለሁሉም ዜጎች ፍትሐዊ፣ አስተማማኝ፣ ዘላቂና ዘመናዊ የኃይል አቅርቦትን ተደራሽ ለማድረግ በሰፊው እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ።

ክቡር ዶ/ር ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ ሥልጠናው በዘርፉ ቀጣይ ዕድገት ላይ ተፅዕኖ ባላቸው አምስት ዋና ዋና ነጥቦች ማለትም አማራጭ የአገልግሎት አቅርቦት ሞዴሎች፣የዋና ግሪድ መድረስ(Grid Arrival)፣የሚኒ-ግሪድ አስተዳደር ፣የኤሌክትሪክ ምርታማ አጠቃቀም፣ፋይናንስ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና መሆኑን ክቡር

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአራተኛ ዙር ከተለዩ 10 ሶላር አስመጪ አዳዲስ ድርጅቶች ጋር የስምምነት ውል ተፈርሟል።

ክቡር ደ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ የብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ትግበራን በዋናነት እየመራና እያስተባበረ የሚገኝ መሆኑን ገልጸው በአሁኑ ወቅት ከዓለም ባንክ በተገኘ የፋይናንስ ድጋፍ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም (ELEAP) እና የገጠር ኤሌክትሪክና መብራት ተደራሽነት ፕሮጀክት (ADELE) በመተግበር ላይ

ዲጂታል የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርን(IWRM) ለማጠናከር የሚያስችል አዳዲስ ሶፍት ዌር ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችል ውይይት ተካሄደ።

ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢታፋ በንግግራቸው የውሃ ሀብት አስተዳደርን በቴክኖሎጂና በዲጂታል መሠረተ-ልማት መደገፍ ወቅታዊና ወሳኝ መሆኑን ገልጸው; ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሀ ሀብት አስተዳደር ትልቁን ድርሻ ሲወጣ የነበረና ስራውን በማገናዘብ ማስተዳደር አስፈላጊ መሆኑን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሀሳብ ሲሰጥበት የነበ

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ የስራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ።

በ2018 ዓ.ም ባለፉት አስር ወራት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኢነርጂ ዘርፉ የታቀዱ ዓበይት ተግባራት፣ የተጠናቀቁ፣ በሂደት ላይ ያሉትንና ያልተጠናቀቁ ተግባራት በቀጣይ ተፈጻሚ የሚሆኑበት መንገድና የነበሩ ውስንነቶችና የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች በጥልቀት ተገምግመዋል።

የውሃ ሃብት አስተዳደር ንዑስ የስራ ቡድን የበጀት ዓመቱን የመጨረሻ የስራ ትግበራ ግምገማ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አካሂዷል።

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተቀናጀ የውሃ ሃብት አስተዳደር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ደበበ ደፈርሶ እንደገለጹት የውሃ ሃብት አስተዳደር ንዑስ የስራ ቡድን የውሃና ኢነርጂ ሴክተር ቡድን አካል የሆነና በውሃ ሃብት አስተዳደር ዘርፍ የሚሰሩትን ተግባራት ለማሳለጥ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፣ ከሴክተር ተቋማትና ሌሎች ስራውን ሊ

የባዘሪኔት ፕሮጀክትን ዲጂታላይዝ ለማድረግ በሚያስችሉ የኮቦቱልቦክስ እና ፓወር ቢአይ ሶፍት ዌር ላይ ስልጠና እየተሠጠ ነው።

በቦታው ተገኝተው የስልጠናውን መርሃ ግብሩ ያስጀመሩት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የቤዚን ፕላን ዴስክ ኃላፊ አቶ አሰግድ አጀመ ስልጠናው የተቀናጀ ውሃ ሀብት አስተዳደር ስር ባለው የባዘር ኔት ፕሮጀክት መዘጋጀቱን ገልጸው በኮቦ ቱል ቦክስ እና ማይክሮሶፍት ፓወር ቢአይ ላይ ያለብንን ክፍተት ለመሙላት ታሳቢ ያደረገ ሲሆን

የህዳሴ ግድብና የቀይ ባህር ዲፕሎማሲ፡ የኢትዮጵያ አዲስ ጂኦፖለቲካዊ ምዕራፍ

ሁለቱም ጉዳዮች ከኢኮኖሚ ጥቅም ባሻገር የአገሪቱን የህልውና ጥያቄ፣ የቀጣናዊ ተጽዕኖ ፈጣሪነት እና የወደፊት የልማት አቅጣጫ የሚወስኑ ናቸው። በእነዚህ መስኮች የተመዘገቡ ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶችም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እና በምሥራቅ አፍሪካ እየተጠናከረ የመጣ የኃይል ማዕከል መሆኗን አመላክተዋል።

የውሃ ሃብትን ለቀጣናዊ ትስስር ማጠናከሪያነት ማዋል እንደሚቻል የሕዳሴ ግድብ ማሳያ ነው

የውሃ ደህንነትን ማረጋገጥ፣ ለሁሉም ተደራሽ የሆነ የንፅህና አጠባበቅ ሥርዓት፣ የማህበረሰብ የመቋቋም አቅም፣ ሳይንስና ኢኖቬሽን፣ ፓን-አፍሪካኒዝም እና አንድነት እንዲሁም ዘላቂ መጻኢ እድል በሚሉ ስድስት ቁልፍ ምሰሶዎች ላይ በስፋት ተመክሯል።

63ኛው የአፍሪካ ቀን ተከበረ።

ኮንፈረንሱ “የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና አስተማማኝ የንፅህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ” /"Assuring Sustainable Water Availability and Safe Sanitation Systems to Achieve the Goals of Agenda 2063"/ በሚል መሪ ቃል የተዘጋ

May 2026

ግዙፉ የገልጨት-ሰሪቴ የውኃ አቅርቦት ፕሮጀክት የህብረተሰቡን ህይወት የሚቀይር ነው። ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮጀክቱ ድርቅን ከመከላከል ባለፈ የሕዝብ ጤናን በማስጠበቅ፣ የነዋሪዎችን መተዳደሪያ አቅም በማጠናከር እና መጪው ትውልድ የሚጠቀምበትን የግብርና እምቅ አቅም በማዘጋጀት ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አመልክተዋል።

በሰብዓዊነት የታጀበ ልማት፡ የአቅመ ደካማ ዜጎች ቤት እድሳትና ግንባታ ውጤታማ ስራዎች፡

በመላው ሀገሪቱ በተለያዩ ክልሎች የነበሩ የፈራረሱ፣ ለዝናብና ለነፋስ ተጋላጭ የሆኑ እና ለኑሮ አስጊ የነበሩ ቤቶች ተጠግነው እንዲሁም አዲስ ተገንብተው ለባለቤቶቻቸው ተረክበዋል። ከዚህ በፊት የሰው ልጅ ሊኖርበት በማይችል ሁኔታ ዝናብን እየተቀበሉ ይኖሩ የነበሩ ቤተሰቦች ዛሬ የተሻለ የመኖሪያ ሁኔታ አግኝተዋል።

ከ34 ቢሊየን ብር በላይ ብድር ለ115 ከተሞች ተሰጠ።

ሚኒስቴሩ በዘርፉ የሚተገብራቸው የድጋፍ ማዕቀፎች በሁለት ዋና አቅጣጫዎች የተደራጁ ሲሆን፣ አንደኛው “ቀጥታ ድጋፍ” ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በኢትዮጵያ የውሃ ፖሊሲ መሠረት “ወጪን በማስመለስ” መርህ ላይ የተመሠረተ የብድር ሥርዓት መሆኑን የውሃ ልማት ፈንድ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዶጊሶ ጎና ገልጸዋል።

ከ88 ሺ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርገው የሾኔ ከተማ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመረቀ።

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ልማት ፈንድ መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዶጊሶ ጎና እንደገለፁት፣ ፕሮጀክቱ የባስኬት ፈንድ ፕሮጀክት አካል ሲሆን የፋይናንስ ድጋፉ ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ፣ ከጣሊያን ልማት ድርጅት እና ከፈረንሳይ ልማት ድርጅት የተገኘ ሲሆን፣ ከ383 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል ብለዋል።

የኢነርጂ ረቂቅ ፖሊሲ ጸደቀ

ፖሊሲው ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም፣ ከአሥር አመቱ የልማት ዕቅድ፣ ከአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ስትራቴጂ፣ ከምዕተ አመቱ የልማት ግቦች እና ከሌሎች ፖሊሲዎች ጋር የተጣጣመ መሆኑ ተገልጿል።

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር በሚሰሩ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተጨባጭ ውጤት እየመጣ ነው ተባለ።

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰምድር ውሃ ፕሮጀክት አካል የሆነው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን የተገነባው የ1ኛ ጤፎ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የምረቃ ስነስርዓት ላይ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር በሚሰሩ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተጨባጭ ውጤት እየመጣ መሆኑ ተገለፀ።

የብሔራዊ ዋን ዋሽ ፕሮግራም (One WASH National Programme - OWNP) ባለፉት ስድስት ዓመታት አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡ ተገለጸ።

የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ አብይ ግርማ አራት ቁልፍ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን ውሃና ኢነርጂ፣ ጤና፣ ትምህርት እና ገንዘብ ሚኒስቴር እንዲሁም የልማት አጋሮችን በማስተባበር በርካታ ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል።

የግድቤን በደጄ የሦስት ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተካሄደ ነው።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአስቸኳይ ጊዜና ልዩ ድጋፍ ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ ሠላማዊት ተወልደ እንደገለፁት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ንጹህ የመጠጥ ውሃን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ከገጸ- ምድርና ከከርሰ -ምድር የውሃ ሃብት በማቅረብ ሰፊ ስራ እየሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜና በጀት በማጠናቀቅ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን እናረጋግጣለን።

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃ አቅርቦት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ታምሩ ገደፋ ተቋሙ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽንን ዘርፍ ለማሻሻል የ10 ዓመታት መሪ ዕቅድ በመንደፍ በተለያዩ ክልሎች የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ ሆኗል ብለዋል።

የሂውማን ካፒታል ኦፕሬሽን (HCO) ፕሮጀክት የባለድርሻ አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።

በሚኒስትር ድኤታ ማዕረግ የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪና የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ የሚኒስትር ድኤታ ተወካይ አቶ ሞቱማ መቃሳ የሂውማን ካፒታል ኦፕሬሽን (HCO)ፕሮጀክት በውሃና ኢነርጂ፣ በትምህርት፣ በግብርና፣ በጤናና በሴቶችና ማሀበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤቶች ቅንጅት፣ ትብብርና በጋራ ዕቅድ የሚተገበርና የሚመራ