የከተሞችን ንፁህና ለእይታ ማራኪ ለማድረግ በትኩረት እንሰራለን፡፡
ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ
የካቲት/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በድሬዳዋ ከተማ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ፣ ማጣሪያና ማስወገጃ የኦፕሬሽንና ጥገና ፕሮጀክት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ባስቀመጡበት ወቅት ከተሞችን ንፁህና ለእይታ ማራኪ ለማድረግ በትኩረት እንሰራለን ብለዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ በመድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ፕሮጀክቱን በዓይነቱ ልዩ የሚያርገው በተለይም በአሁኑ ወቅት መንግስት ከተሞችን ንፁህና ለእይታ ማራኪ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ከሚያከናውናቸው ተግባራት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡ አክለውም ክቡር ሚኒስትሩ ፕሮጀክቱ ትልልቅ በሆኑ ከተሞች በመቀሌ፣ በአዳማ ፣ ድሬደዋ፣ አዋሳና ባህርዳር የሚተገበር ሲሆን ሁለቱ የመሠረት ድንጋይ ተቀምጦ ስራ ጀምረዋል ድሬደዋ ዛሬ አስቀምጠናል በቀጣይ አዋሳና ባህርዳር የሚቀጥሉ ይሆናሉ ብለዋል። የፕሮጀክቱ ግንባታ በአከባቢው ለሚገኙ ሴቶችና ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥር ሊሆን ይገባዋል ሲሉ ለኮንትራክተሩ አሳስበዋል። አያይዘውም የድሬዳዋን ህዝብ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ስራው በፍጥነትና በጥራት ተጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥም አሳስበዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በሁለተኛ ከተሞች በመጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ፕሮግራም ለሃያ ሶስት ከተሞች በተያዘው ፕሮግራም በብርና በዶላር በድምሩ በብር ወደ 1.3 ቢሊዩን በሚገመት ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የሚገነባ ነው፡፡