የአንድ ቋት ብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም የሁለተኛው ፌዝ የመስክ ሱፐርቪዥን በሁሉም ክልሎች እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡

የአንድ ቋት ብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም የሁለተኛው ፌዝ የመስክ ሱፐርቪዥን በሁሉም ክልሎች እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡   የካቲት 9/2018 ዓም (ው.ኢ.ሚ) የአንድ ቋት ብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም የሁለተኛው ፌዝ የመስክ ሱፐርቪዥን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተሳተፉበት ሁኔታ በሁሉም ክልሎች እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡ የሱፐርቪዥን ስምሪት ቅድመ ዝግጅቱን አስመልክቶ በተካሄደ መድረክ የተገኙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሚኒስትር ዲኤታ ማእረግ የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ሞቱማ መቃሳ (ተወካይ) የአንድ ቋት ብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም የሁለተኛው ፌዝ የስራ የመስክ ግምገማ እንደሚሄድ ገልጸዋል፡፡   የCWA II የትግበራ ሂደትን እና ሰፊውን የOWNP ግምገማ፣ቁልፍ ስኬቶችን፣ ተግዳሮቶችን እና የተማሩትን ትምህርቶች መለየት፣በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ ክልሎች እና አጋሮች መካከል ቅንጅትን ማጠናከር እና ዘላቂ፣ ሁሉን አቀፍ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የዋሽ አገልግሎት አቅርቦትን ለማፋጠን ቅድሚያ እንደሚሰጣቸውም አቶ ሞቱማ ገልጸዋል፡፡ ከሁሉም ክልሎ በተሰሩ ስራዎች ላይ የቀረቡ ሪፖርቶችን በመመልከት ወደ መስክ ስትወርዱ ስራዎችን በግንባር በማየትና በመገምገም በቀጣይ ስራዎቹ በተያዘላቸው ወቅት እንዲጠናቀቁ ሊያግዝ የሚችል ሪፖርት እንደምታቀርቡ ተስፋ አደርጋለሁም ብለዋል፡፡   የብሔራዊ ዋን ዋሽ አስተባባሪ አቶ አብይ ግርማ በዚህ ተልእኮ ከፌደራል ጀምሮ ያሉ ሴክተሮች ያለውን የስራ አፈጻጸም በመገምገምና ቡድኑም ወደ መስክ በመውረድ እስካሁን የተካሄደውን አፈጻጸም በመገምግም ወደ ኋላ የቀሩትን ችግሮች በመለየትና በመፍታት፣ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ፕሮግራሙ በተያዘለት ጊዜ እንዲያልቅ እንደሚረዳ አውስተው፤ ተልእኮው በመስክ በመገኘት በሁሉም ክልሎች እንደሚታይ በመግለጽ በቀጣይ ማጠቃለያ ሪፖርት እንደሚቀርብ ገልጸዋል፡፡   በመጨረሻም አቶ አብይ ስራውን ከሚመለከታቸው ሴክተሮች ማለትም ከውሃ፣ ከጤና፣ ከትምህርት፣ ከፋይናንስ እንዲሁም ፕሮግራሙን ከሚደግፉ አጋር ድርጅቶች፤ አለም ባንክ፣ የእንግሊዝ መንግስት፣ ዩኒሴፍ፤ ጋር በመሆን ግባችን ያለፈውን አፈፃፀም መገምገም ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱ መንገዱን በማጽዳት የስርዓት ማነቆዎች በመፍታት የCWA IIን ስኬት በማረጋገጥ ወደ ሚቀጥለው የፕሮግራሙ ምዕራፍ ለመቀጠል እየተሰራ እንደሆን ገልጸዋል፡፡ በመርሀ ግብሩ ላይ ከውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣CWA II የልማት አጋሮች እና የዋሽ ዘርፍ ሚኒስትሮች የተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም አስተባባሪዎች ተሳትፈውበታል፡፡

Share this Post