7.3 ሚሊዬን ብር በሚጠጋ ወጪ ባለ ብዙ መንደር የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የግንባታ ቁጥጥር እና የማማከር ስራ የውል ስምምነት ተፈረመ፡፡

7.3 ሚሊዬን ብር በሚጠጋ ወጪ ባለ ብዙ መንደር የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የግንባታ ቁጥጥር እና የማማከር ስራ የውል ስምምነት ተፈረመ፡፡ ሰኔ 13/2017 ዓ/ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር 7.3 ሚሊዬን ብር በሚጠጋ ወጪ ባለ ብዙ መንደር የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የግንባታ ቁጥጥር እና የማማከር ስራ የውል ስምምነት ከደቡብ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት ጋር ተፈራረመ፡፡ የውል ስምምነቱን የተፈራረሙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ በመጠጥ ውሃ ስራ የዲዛይንና የግንባታ ምዕራፍ ዋነኛውና መሰረታዊ ጉዳይ በመሆኑና የአካባበቢውን ማህበረሰብ በአጭር ጊዜ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ በከፍተኛ ትኩረትና ጥንቃቄ በመተግበር በታቀደው ጊዜ፣ ጥራትና ፍጥነት እንዲጠናቀቅ መደረግ አለበት ብለዋል ። የደቡብ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት ስራ አስኪያጅ ኢ/ር አብዲሳ ኩፎ በገቡት ውል መሠረት የተረከቡትን ስራና ሀላፊነት በከፍተኛ ጥንቃቄ እና ከታቀደው ጊዜ በፊት በማጠናቀቅ ለማስረከብ ጥረት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል። የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ የሚተገበረው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በቡርጂ ዞን በሶያማ መንደር ሲሆን ፕሮጀክቱ የሲ አር ዋሽ አካል እንደሆነና የበጀቱ ምንጭ የዋን ዋሽ ብሔራዊ ፕሮግራም መሆኑም ተገልጿል። የግንባታ ጊዜው የሚጠናቀቀው በ12ወራት መሆኑ በውል ስምምነቱ ተገልጿል።

Share this Post