2017 ዓም ዘመን ተሸጋሪ ስራዎች የታዩበትና ህዳሴን የጨረስንበት የማንሰራራት ዘመን መሆኑ ተገለጸ።
2017 ዓም ዘመን ተሸጋሪ ስራዎች የታዩበትና ህዳሴን የጨረስንበት የማንሰራራት ዘመን መሆኑ ተገለጸ።
ሐምሌ 16/2017ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2017 የበጀት ዓመት ማጠቃለያ እና የመቶ ቀናት ሀገራዊ አፈጻጸም እና 2018 ዓም እቅድ ላይ ከሰራተኞች ጋር ተወያዬ።
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ አለሙ መንገሻ የ2017 በጀት ዓመት ማጠቃለያ እና የመቶ ቀናት ሀገራዊ አፈጻጸም፤ 2018 ዓም እቅድ አለም አቀፍ የኢኮኖሚ አዝማሚያ የመሰረተ ልማት ዘርፍ ዕቅድ፣ የማክሮኢኮኖሚ ዕቅድ፣ የማህበራዊ ልማትና የህዝብ አገልግሎት፣ የኢኮኖሚ ዘርፎች ዕቅድ፣ ሠላም፣ ፍትሕና ዲፕሎማሲ ዘርፍ ዕቅድ እንዲሁም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ማጠቃለያ ሪፖርትና የ2018 ዓ.ም እቅድን በንጽጽር በማቅረብ የበጀት አመቱን የጸደቀ በጀትም ካለፉት አመታት የተሸለ መሆኑን በሪፖርታቸው አቅርበዋል፡፡
የውይይት መድረኩን የመሩት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በመድረኩ የ2017ዓ.ም የበጀት ዓመት ማጠቃለያ እና የመቶ ቀናት ሀገራዊ አፈጻጸም እና 2018 ዓም እቅድ ዋና ዋና ተግባራት እንደ ሀገር ምን አቅደን፣ ምን እንዳሳካን፣ እያየን የመጣን ሲሆን፤ በተለይ 2017 ዓ.ም ልዩ የሚያደርገው ብዙ ነገሮችን የቀየርንበትና ህዳሴን የጨረስንበት የማንሰራራት ዘመን መሆኑን ነው ብለዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው 2017 ዓም ዘመን ተሸጋሪ ስራዎች የታዩበት መሆኑን በመግለጽ በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ በውይይት ለተነሱ ጥያቄዎች፣ ሀሳብና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያም ሰጥተዋል።
በመጨረሻም በቀጣይ የተቋሙን እቅድ በተሻለ እውቀትና የመፈፀም አቅም ለማሳካት ሰራተኛው የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ክቡር ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡
በእለቱ የተቋሙ ሰራተኞች የተሳተፉበት የደም ልገሳ መርሃግብር ተካሂዷል፡፡