ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ከዋተር ኤድ (Water Aid) ሉኡካን ጋር ተወያዩ።

ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ከዋተር ኤድ (Water Aid) ሉኡካን ጋር ተወያዩ። ሰኔ 10/2017ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ከዋተር ኤድ ልኡክ ጋር በጋራ በሚሰሯቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል። ክቡር አምባሳደሩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በውሃ ሀብት አስተዳደር ፣ በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን እንዲሁም በኢነርጂ ልማት ዘርፉ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ላለፉት አራት ዓመታት በተሠራው ስራ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን 72 በመቶ ማድረስ መቻሉና በሀይል አቅርቦቱም ከ60በመቶ ያልበለጡ ኢትዮጵያውያንን ተደራሽ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። እንደ ሀገር በገጠርም ሆነ በከተማ የተለያየ የውሃ ሽፋን ቢኖርም በተቻለ መጠን ተደራሽነትን ለማስፋት በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም ነው ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው የገለጹት። አክለውም በዘርፉ ውጤታማ ስራ ለመስራምት በፖሊሲ የተደገፈ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ በሚያሳድግና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጠንካራ ስራ እየተሰራ ቢሆንም ገና ያልደረስንባቸውና ልንተገብራቸው የሚገቡ በርካታ የቤት ስራዎች አሉብን ብለዋል። አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚኖረው በገጠር እና በተበታተነ አሰፋፈር መሆኑ፣ የህዝብ ቁጥር መጨመር፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ተያያዠ ችግሮች በሚፈለገው ልክ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽንን ተደራሽ ለማድግ ትልቅ እንቅፋቶች መሆናቸውንም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ለልኡካኑ አስረድተዋል። ወተር ኤድም በዘርፉ የሚያደረገውን ከአቅም ግንባታ፣ ዜጎች ንጹህ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት እንዲያገኙ ጥሩ አበርከቶ ያደረጉ በመሆኑ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አመስግነዋል። የWater Aid UK ዋና ስራ አስፈጻሚ Mr.Tim Wainwright ኢትዮጵያ በዋተር ኤድ ትልቅ ትኩረት ከተሰጣቸው አገሮች ተርታ መሆኗን ጠቅሰው የዋን ዋሽ ፕሮግራም አፈጻጸምም እንደ ሀገር በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኑ የሚደነቅ መሆኑንና ከዚህም በላይ ብዙ እንደሚጠብቁ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። እንደ አጋርነነታቸውም በሙሉ አቅም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉና በዚህ ረገድም ከአለም ባንክ ጋር በቅርበት እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። ውሃና ሳኒቴሽን የሚነጣጠሉ አይደሉም ያሉት Mr.Tim ሁለቱንም አስተሳስረን ከዘርፉ አንጻር ያሉ ችግሮችን ዳሠሳ በመስራት ግልጽ ርምጃ በመውሰድ አጋርነታችን እናጠናክራለን ፤ ለዚህ ደግሞ በጋራ ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል። ወተር ኤድ በዩናይትድ ኪንግ ደም (UK) የተቋቋመ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን

Share this Post