የዩኤን ዲፒ (UNDP)ስቲሪንግ ኮሚቴ በፕሮጀክቱ እስካሁን በተሰሩ ስራዎችና በወደፊት አቅጣጫ ላይ ውይይት አደረገ።

የዩኤን ዲፒ (UNDP) ስቲሪንግ ኮሚቴ በፕሮጀክቱ እስካሁን በተሰሩ ስራዎችና በወደፊት አቅጣጫ ላይ ውይይት አደረገ ። ህዳር 08/2018 ዓ/ም (ውኢሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የዩኤንዲፒ/UNDP/አፍሪካ ሚኒግሪድ ፕሮግራም ስቲሪንግ /String/ኮሚቴ በፕሮጀክቱ እስካሁን በተሰሩ ስራዎች፣ በተዘረጉ አስቻይ ሁኔታዎች፣ በመጡ ለውጦችና በወደፊት አቅጣጫ ላይ ውይይት አድርጓል።   የውይይት መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ኢንጅነር ሱልጣን ወሊ እንደሀገር ከዋናው የኤሌክትሪክ መስመር ርቀው ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ሶላር ሚኒ ግሪድን ጨምሮ በተለያዩ ቴክኖሎጂዎች የኤሌክትሪክ ሀይል ተጠቃሚ ለማድረግ ሰፊ ስራ እየተሰራ እንዳለና ከፍተኛ ውጤት የታየበት መሆኑን ገልፀው የእስቲሪንግ/String/ኮሚቴው ውይይት ለፕሮጀክቱ ውጤታማነት አስቻይ ሁኔታዎችን ለማጠናከር የሚያግዝ ነው ብለዋል።   ክቡር ሚኒስትር ድኤታ አክለው እስካሁን በፕሮጀክቱ ለ50 ከመንግስትና ከግል ድርጅቶች ለተመለመሉ መሃንድሶችና ለ400 መቶ ሴቶች ከአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በሶላር ሚኒግሪድ ዝርጋታ፣ አጠቃቀም፣ ኦፕሬሽንና ጥገና ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠትና ግንዛቤ በመፍጠር ለፕሮጀክቱ ተግባራዊነትና ውጤታማነት አስቻይ ሁኔታ እንደተፈጠረ አብራርተዋል።   ዶ/ር ሱልጣን በንግግራቸው በፕሮጀክቱ በ2019 ዓ/ም መጨረሻ የሚጠናቀቅና አገልግሎት የሚሰጥ በ3 ክልሎች በሶማሌ ሀሬ ቀበሌ 70 ኪሎ ዋት፣ በኦሮሚያ ሰርባ ቀበሌ 90 ኪሎ ዋት እና በትግራይ ፈዱስ ቀበሌ 147 ኪሎ ዋትእና በሌሎችም አካባቢዎች እንደ አንገብጋቢነቱ እንደ በጀቱ ሁኔታና እደተጫራቾቹ ብቃት ታይቶ ቅድሚያ እየተሰጠ የሚገነባ በአጠቃላይ 624 ኪ.ዋ የሚያመነጭና 31625 የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ የሚያደርግ ሶላር ሚኒግሪድ ለመገንባት እንደታቀደም ገልፀዋል።   በውይይት መድረኩ በፕሮጀክቱ አስተባባሪ፣ ባለሙያዎችና በሌሎችም በሚመለከታቸው አካላት እስካሁን በፕሮጀክቱ አተገባበርና ውጤታማነት ላይ የተሰሩና የተዘረጉ አስቻይ ሁኔታዎች፣ የ2026 የስራ ዕቅድና ለመገንባት የታቀዱ የሶላር ሚኒግሬዶች ብዛትና አድራሻ ምን እንደሚመስልና የት እንደሆነ በሰነድ ቀርቦ ከኮሚቴው አባላት አስተያየትና ጥያቄዎች ተነስተው ከተወያዩበት በኋላ ዶ/ር ሱልጣን ምላሽና ማበብራሪያ ሰጥተዋል። በፕሮጀክቱ እስካሁን የተሰሩ ስራዎች ሶላር ሚኒግሪድና ሌሎችም ታዳሽ ቴክኖሎጂዎችን ለመዘርጋት ለመጠቀም፣ ለመጠገንና ለመላመድ የሚያበቃ የግንዛቤና የአቅም ግንባታ ስራዎችን በመስራት አስቻይና ምቹ ሁኔታን መፍጠር እንደተቻለ በመድረኩ ተገልጿል ።

Share this Post