በከርሰ ምድር ውሃ ምርምር፣ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ እና ማገገም (Rehabilitation) ምህድስና ላይ ያተኮረ አለም አቀፍ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በከርሰ ምድር ውሃ ምርምር፣ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ እና ማገገም (Rehabilitation) ምህድስና ላይ ያተኮረ አለም አቀፍ ስልጠና እየተሰጠ ነው። ሰኔ 16/2017 ዓ/ም በከርሰ ምድር ውሃ ምርምር፣ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ እና ማገገም ምህድስና ላይ ያተኮረ በኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት አለምአቀፍ ስልጠና እየተሰጠ ነው። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ከሱዳን የመጡ ሰልጠኞችን እንኳን ዳህና መጣችሁ ካሉ በኋላ የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩት ከስልጠና በሻገር የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል ራዕይ እውን በማድረግ በውሃ ሴክተር ተጨባጭ መፍትሔ የሚያመጣ የፓሊሲ እና የፈጠራ ሀሳብ ማመንጨት የሚያስችል ተቋም ሆኖ የሚያገለግል ነው ብለዋል። ክቡር ሚኒስቴር ዴኤታው ዘላቂ የውሃ ሀብት ልማት ላይ በጋራ በመተባበር መሥራት ከቻልን የውሃ ደህንነትን በማረጋገጥ ሁሉንም ተጠቃሚ መድረግ እንደሚቻል ለሰልጣኞች መልዕክት አስተላልፈዋል ። የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ዶ/ር መለስ አለም በከርሰ ምድር ውሃ ምርምር ቁፋሮ ኢትዮጵያ በአቅም ግንባታ ዘርፉ ለአፍሪካ ወንድሞች ስልጠና መስጠቷ መልካም ጅምር መሆኑን ገልፀው ፣ ኢትዮጵያ በንጉሱ ኃ/ስላሴ ዘመን ኔልሰን ማንዴላን ማሰልጠኗን በማሳያነት ገልጸዋል ። ከሱዳን መንግሥት ጋር የረጅም ጊዜ ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት መኖሩን የገለጹት ክቡር አምባሳደሩ የሱዳን መረጋጋት ለኢትዮጵያ መረጋጋትም መልካም በመሆኑ ኢትዮጰያ ከልብ የመነጨ ድጋፍ እንደምታደርግ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ከጀመረችው የኃይል መሠረተ ልማት ትስስር በተጨማሪ በአቅም ግንባታ ዘርፉም የጀመረችው መልካም ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል። የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ታመነ ሀይሉ በበኩላቸው በስልጠናው ላይ ከክልሎች እና ከሱዳን መንግስት የተውጣጡ የውሃ ባለሙያዎች የሚሳተፋ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ አለም አቀፋዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት አቅም መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል ። ተቋሙ ከዚህ በፊት ለ18 የአፍሪካ ሀገራት አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስልጠና መሰጠቱን ገልፀው ፣ ናጄሪያ ፣ ማላዊ፣ ኬኒያ ፣ ታንዛኒያ ፣ ሱማሊያ እና ሱዳን ተሳታፊዎች እንደነበሩ ዋና ዳይሬክተሩ አመላክተዋል። የጃፓን አለም አቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ ተወካይ Mr ኦሺማ ከንሱኬ የጃፓን መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር በግብርና ፣ በኢንዳስትሪ ፣ በጤና እና በውሃ ልማት ላይ ለረጅም ጊዜ በትብብር መሥራቱን ገልፀው ፣ በቀጣይም በውሃ ሴክተር ላይ የአቅም ግንባታ ስራውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል ። ስልጠናው ለ3 ሳምንታት የሚቆይ ሲሆን በከርሰ ምድር ውሃ ምርምር ፣ የጉድጓድ ውሃ ቁፋሮ ምህንድስና እና የነባሩን ጉድጓድ ማገገም ( Rehabilitation ) ላይ ያተኮረ እና በዘርፉ ያለውን የአቅም ውስንነት መፍትሔ የሚያስገኝ ነው ተብሏል ።

Share this Post