የሦስተኛው ምዕራፍ OWNP-CWA III የዝግጅት ምእራፍ ላይ ውይይት ተካሄደ።
የሦስተኛው ምዕራፍ OWNP-CWA III የዝግጅት ምእራፍ ላይ ውይይት ተካሄደ።
ነሐሴ 27/2018ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) አዲስ አበባ OWNP-CWA III በኢትዮጵያ በሙሉ ዘላቂ እና ፍትሃዊ የውሃ፣ የንፅህና እና የንፅህና መጠበቂያ (WaSH) አገልግሎቶችን ተዳራሽነ በሚያረጋግጠው ፌዝ 3 ዋሽ ፕሮግራም የዝግጅት ላይ ውይይት ተካሄደ።
መርሀግብሩ ላይ የተገኙት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ዶክተር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ባደረጉት ንግግር የፕሮግራሙን ዋና ዓላማ አጠቃላይ ንድፍ የበለጠ ለማሻሻል እና ለማጠናከር መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም በፕሮግራሙ ወሰንና ሽፋን፣ የውጤት መስኮች፣ የፋይናንስ ክፍያ አመልካቾች ፣የክትትልና ግምገማ ስርዓቶች እንዲሁም አፈፃፀም ላይ የጋራ ስምምነት ላይ ለመድረስ ያለመ መሆኑንም ጠቅሰዋል ።
ሚኒስትር ዲኤታው በማከል ባለፋት ቀናት ላይ የመንግሥት እና የልማት አጋሮች ቡድኖች ከፌዴራል የዋሽ ሴክተር ጋር በመሆን ስኬቶችን የመገምገም እና የስትራቴጂክ አቅጣጫዎችን የመለየት ስራ ማከናወናቸውን ገልጸዋል ።
በውይይቱ ላይም የቴክኒክ፣ የሕዝብ ወጪ፣ (የፋይናንስ አስተዳደር) እንዲሁም የአካባቢ እና ማህበራዊ ስርዓቶች ምዘና ግኝቶችና የውሳኔ ሃሳቦች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው በመጥቀስ OWNP-CWA III በኢትዮጵያ በሙሉ ዘላቂ እና ፍትሃዊ የውሃ፣ የንፅህና እና የንፅህና መጠበቂያ (WaSH) አገልግሎቶችን ተዳራሽነት ለማፋጠን ታስቦ የተዘጋጀ ነውም ብለዋል።
በመጨረሻም ክቡር አምባሳደር አስፋው የዚህ ፕሮግራም ስኬት በጋራ ቁርጠኝነትና ባለቤትነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን በመጠቆም ሁሉም ተሳታፊዎች በሚያደርጉት ንቁ ተሳትፎ ፕሮግራሙ በተያዘለት ጊዜ ወደ ትግበራ እንዲገባ ጥሪ አቅርበዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የቀጣዩን የOWNP-III ፕሮግራም ዲዛይን ለማጠናከር፣ ከተሳታፊዎች ግብዓት ለማሰባሰብ እና በተካሄዱ የቴክኒክ፣ የህዝብ ወጪ፣ የፋይናንሻል ሥርዓት፣ የአካባቢና ማህበራዊ ሥርዓት ግምገማዎች የተገኙ ግኝቶችን ወደ ፕሮግራሙ ዲዛይን ማካተት በሚያስችሉ ጉዳዮች በተለያዩ አካላት ሰነዶች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በመጨረሻም የውይይቱ ውጤቶችና ከተሳታፊዎች የተሰበሰቡ ግብዓቶች ቀጣዩን የOWNP-III ፕሮግራም ለማጠናቀቅ እንደ ጠቃሚ ግብዓት እንደሚያገለግሉ የተገለፀ ሲሆን የፕሮግራም ዝግጅቱን ለማስቀጠል ቀጣይ እርምጃዎችም ተመላክተዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የፌደራል ሚኒስቴር መስሪያቤት፣ የክልል ውሃ፣ ጤና፣ ፋይናንስ እና ትምህርት ቢሮዎች፣ የልማት አጋሮች እና የቴክኒክ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል ።
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto