ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ የአለም አቀፍ የሶላር አሊያንስ (ISA) ዋና ዳይሬክተርን እና ልኡካኑን ተቀብለው አነጋገሩ።

የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ የአለም አቀፍ የሶላር አሊያንስ (ISA) ዋና ዳይሬክተርን እና ልኡካኑን ተቀብለው አነጋገሩ። ነሀሴ 6/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአለም አቀፍ ሶላር አሊያንስ (ISA) ጋር ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር ማሳደግ እና በዓለም አቀፍ የፀሐይ ሀይል በሚተገበሩ እና እየተተገበሩ ባሉ የ 400 ሜጋ ዋት የፀሐይ ፓርክን ፣ የ700ኪሎዋት የሶላር ሚኒ ግሪድ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ፣ Solar Water Pump ለመስኖ እና ለመጠጥ ውሃ አቅርቦት በመጠቀም በኢትዮጵያ የፀሐይ ኃይልን ለማስፋፋት የፋይናንስ እና የቴክኖሎጂ ትብብር እድሎችን ማመቻቸት ላይ ተወያይተዋል ። ልኡካኑ በቀጣይ ሁለት ቀናት በሚኖራቸው ቆይታ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በጋራ በሚሰሯቸው ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ።

Share this Post