ከቻይና ኤግዚም ባንክ (Exim Bank) የ100 ሚሊየን ዶላር ብድር ለማግኘት የሚያስችል የትብብር የመግባቢያ የውል ስምምነት ተፈረመ።
ሐምሌ 29/2017 ዓ/ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከቻይና ኤግዚም ባንክ የ100 ሚሊየን ዶላር ብድር ለማግኘት የሚያስችለውን የትብብር የመግባቢያ የውል ስምምነት የብድር አመቻች ከሆነው ሲጂሲኦሲ (CGCOC) ድርጅት ጋር ተፈራረመ።
የውል ስምምነቱን የፈረሙት ክቡር ዶ/ር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ብድሩ ሲገኝ በአምስት ከተሞች የመጠጥ ውሃና የሳኒቴሽ መሠረተ ልማት ግንባታን ለማከናወን መታቀዱን ገልፀዋል ።
ከቻይና መንግስት ጋር በትብብር የመስራት ዕድል መገኘቱ መልካም አጋጣሚ ነው ያሉት መልካም አገጣሚ ነው ያሉት ክቡር አምባሳደሩ በቀጣይ በትብብር ለሚሰሩ ስራዎችም ጥሩ መደላድል ይፈጥራል ብለዋል።
በብድር በሚገኘው ገንዘብ በኦሮሚያ ክልል ሆለታ ከተማ፣በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አረካ ከተማ፣ በማዕከላዊ ክልል በኢንሴኖና ጦራ ከተሞች እና በደቡብ ምዕራብ ክልል ሚዛን አማን ከተማ የመጠጥ ውሃና የሳኒቴሽን መሠረተ ልማት ለመገንባት መታቀዱን ክቡር አምባሳደሩ ገልጸዋል።