የአፍሪካ የኢኮሃይድሮሎጂ ቀጠናዊ ማዕከል (ARCE) በዩኔስኮ ተገመገመ ።
የአፍሪካ የኢኮሃይድሮሎጂ ቀጠናዊ ማዕከል (ARCE) በዩኔስኮ ተገመገመ ።
በኢትዮጵያ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአፍሪካ የኢኮሃይድሮሎጂ ቀጠናዊ ማዕከል (ARCE) በዩኔስኮ ግምገማ ተካሄደ።
ነሐሴ 20/2018ዓም (ው.ኢ.ሚ)
በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሃብት ዘርፍ ሚ/ር ዲኤታ ተወካይ እና በሚኒስትር ዲኤታ ማእረግ የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳ እንደገለጹት፤ማዕከሉ በኢትዮጵያ መንግስት እና በዩኔስኮ መካከል በተደረገ ስምምነት ከተቋቋመ ወዲህ በምርምር፣ በአቅም ግንባታ፣ በዕውቀት ሽግግር እና በቴክኒክ ትብብር ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸዋል።
ክቡር አቶ ሞቱማ በማከል ማዕከሉ ለተፋሰስ ጥበቃ፣ ለስነ-ምህዳር ማገገም፣ ለውሃ ጥራት መሻሻል፣ ለብዝሃ-ሕይወት ጥበቃና ለአየር ንብረት መቋቋም እና ዘላቂ ኑሮ እንደ ተግባራዊ ላቦራቶሪ የሚያገለግሉ 11 የኢኮሃይድሮሎጂ ማሳያ ጣቢያዎችን ገንብቶ ወደ ሥራ ማስገባንም አውስተዋል።
በኢትዮጵያ መንግስት እና በዩኔስኮ ስምምነት መሰረት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ በራስ ገዝ የፌደራል ተቋምነት የተቋቋመው ማዕከሉ፤ በሳይንሳዊ ዕውቀት ላይ የተመሰረቱ መፍትሔዎችን ወደ ተግባር በመቀየር ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛልም ብለዋል።
ማዕከሉ የዩኔስኮ የዓለም አቀፍ ሃይድሮሎጂ ፕሮግራም አካል በመሆን በአፍሪካ ደረጃ የሚከሰቱ የውሃ ክፍተቶችን ለመቅረፍና ለስነ-ምህዳር እንክብካቤ የሚደረገውን ጥረት የሚያጠናክር ቀጠናዊ ማዕከል ሆኖ እንደሚቀጥልም ክቡር አቶ ሞቱማ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለማዕከሉ መታደስና መጠናከር ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግና ከተገምጋሚው ቡድን የሚወጡ አስተያየቶችና ምክረ-ሃሳቦች ተቋሙን የበለጠ ውጤታማ እንደሚያደርጉት ጠቅሰዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ ባለፉት ስድት ዓመት የተሰሩ እና ውጤት ያስመዘገቡ ስራዎችን አቶ ዮሀንስ ዘሩሁን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
ከዩኒስኮ የመጡ ተወካዮችም በቀረበላቸው ገለጻ በመነሳት ማእከሉ ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሀሳብ አስተያየታቸውን ሰጥተዋ፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ የውሃና ኢነርጂ ከፍተኛ
አመራች የዘርፉ ባለሙያዎች፣የዩኒስኮ ተወካዮችና ዩኒቨርስቲዎች ተሳትፈዋል፡፡
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto