ለአቅመ ደካማ ተማሪዎች ድጋፍ የሚደረግ 6144 ደብተር ተበረከተ፡፡

ለአቅመ ደካማ ተማሪዎች ድጋፍ የሚደረግ 6144 ደብተር ተበረከተ፡፡

ሐምሌ 18/2017 ዓ/ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለ2017 ዓ/ም ለክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የሚውል የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ የሚውል 32 ካርቶን ደብተር በኮንትራክተሮች ተበርክቷል፡፡

ድጋፍን ያደረጉት የኢትዮጵያ የውሃ ኮንትራክተሮች ማህበር አባላት ሲሆኑ፤ ድጋፍ ያደረጉት የማህበሩ አባላትም ጂቲቢ ኢንጂነሪንግ 8 ካርቶን ደብተር፤ እሙ ጠቅላላ አስመጪ 8 ካርቶን ደብተር፤ የወገሬት ኮነስትራክሽን 8 ካርቶን ደብተር፤ እንዲሁም የባይጌታ ብዝነስ 8 ካርቶን ደብተር አበርክተዋል፡፡

በጠቅላላ 6144 ደብተሮ ተበርክተዋል፡፡

በርክክቡ ወቅት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ድጋፍ ያደረጉትን የማህበሩን አባላት በሙሉ አመስግነው ሀገር የምትገነባው እንዲህ በጋራ ተባብረን ስንሰራ ነው ብለዋል፡፡

የማህበሩ ሊቀመንበር ኢ/ር ጌታሁን ታገሰ በበኩላቸው ትውልድን መደገፍና ማብቃት የሁሉም ዜጋ ሃላፊነት መሆኑን ገልጸው፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ላደረገላቸው ጥሪ አመስግነዋል፡፡

ወደፊትም አብረው እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

የተቋማቱ አመራሮች በውሃና ኢኒርጂ በመገኝት ርክክቡን ፈጽመዋል፡፡

Share this Post