ከ472.4 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮና ግንባታ ሥራ የውል ስምምነት ተፈረመ።
ከ472.4 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮና ግንባታ ሥራ የውል ስምምነት ተፈረመ።
ነሐሴ 1/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ.) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ከሶፍ ኡመር ንግድና ግንባታ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ጋር በጠቅላላ 472,498,326.50 (አራት መቶ ሰባ ሁለት ሚሊዮን አራት መቶ ዘጠና ስምንት ሺህ ሦስት መቶ ሃያ ስድስት ብር ከ50 ሳንቲም) ወጪ የሚከናወን የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮና ግንባታ ሥራ የውል ስምምነት ፈርመዋል።
የውሉ ስምምነት በኦሮሚያ ክልል ቄሌም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሳዳሌ ወረዳ፣ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ሊበን እና ገላን ወረዳዎች የሚገኙ በአጠቃላይ ሰባት የውሃ ፕሮጀክቶችን ለማስፈጸም የተደረገ ሲሆን፣ ፕሮጀክቶቹ የውሃ አገልግሎትን በማስፋፋት የኅብረተሰቡን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት በማሻሻል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል።
እነዚህ ፕሮጀክቶች በዓለም ባንክ ድጋፍ በሚተገበረው የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት (Horn of Africa Groundwater for Resilience Project) አካል ሲሆኑ፣ በአካባቢዎቹ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን በማጠናከር፣ የድርቅ ተጽእኖን በመቀነስና የኅብረተሰቡን ኑሮ በማሻሻል ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚጫወቱ ይጠበቃል።
በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ እንደገለጹት፣ ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው ከሦስት እስከ አራት ወራት ጊዜ ውስጥ በጥራት ተጠናቀው ለማኅበረሰቡ አገልግሎት እንዲውሉ በትኩረት መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል።
ክቡር አምባሳደሩ በተጨማሪም ውሉን የወሰደው ድርጅት የጥራት መስፈርቶችን በሙሉ በማሟላት፣ የፕሮጀክቱን የጊዜ ሰሌዳ በማክበር ለሕዝብ ዘላቂ ጥቅም የሚያስገኝ ሥራ እንዲያከናውን አሳስበው፣ ሚኒስቴሩም የፕሮጀክቶቹን አፈጻጸም በቅርበት እንደሚከታተል ገልጸዋል።
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto