የባስኬት ፈንድ ፕሮግራም 43 ከተሞችን ንፁህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

የባስኬት ፈንድ ፕሮግራም 43 ከተሞችን ንፁህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

አዳማ:-ሰኔ 12/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በውሃ ልማት ፈንድ በኩል የሚተገበረው የባስኬት ፈንድ ፕሮግራም የማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ በባስኬት ፈንድ ፕሮግራም 43 ከተሞችን ንፁህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ ተገለፀ።

የባስኬት ፈንድ ፕሮግራም በጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ /AICS/ በፈረንሳይ ልማት ድርጅት /AFD/ እና በአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ /EIB/ የገንዘብ ድጋፍ ሲተገበር የነበረው በ43 ከተሞች ላይ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ማጠቃለያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ የማቺንግ ፈንድ ፕሮግራም እ.ኤ.አ በ2016 ስንጀምር የጋራ ራዕያችን ለማሳካት በፍጥነት በማደግ ላይ ለሚገኙ ትንንሽ እና መካከለኛ ከተሞችን ለማቋቋም ዘላቂ የውሃ እና የንፅህና አጠባበቅ ስርዓት ለመገንባት ያለመ ነበር ብለዋል።

ክቡር አምባሳደር አያይዘውም ከፕሮግራሙ ምስረታ ጀምሮ በፕሮጀክቶች ትግበራ ወቅት አስቸጋሪ የሚያደርጉ ውስብስብ ሀገራዊ የፀጥታ ጉዳዮችና የዋጋ ግሽበቱን ተቋቁመን ውጤታማ ስራዎችን በመስራት ክልሎችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

ከጀመርናቸው 43 የከተማ ፕሮጀክቶች ውስጥ 40ዎቹ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ወደ ስራ የገቡ ሲሆን ቀሪዎቹ 3ቱ ደግሞ በቅርቡ ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ ያሉት ክቡር አምባሳደር በኢትዮጵያ በ7 ክልሎች በሚገኙ 43 ከተሞች ወደ 2.1 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ንፁህ እና አስተማማኝ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ሆነዋል ብለዋል።

ክቡር አምባሳደር አክለውም በንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት የህብረተሰቡን ጤና እንዲሻሻል በማድረግ የንፅህና አጠባበቅንም ጨምሮ ለሚሊዮኖች ህይወት ለውጥ ማምጣት መቻላችን የጋራ ስኬቶቻችን ናቸውም ብለዋል።

የጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ /AICS/ እና የፈረንሳይ ልማት ድርጅት /AFD/ ተወካዮች በመድረኩ ላይ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በአቅም ግንባታ እና በቴክኒካል ድጋፍ ዙሪያ የነበራቸውን ቆይታና ለፕሮጀክቱ ተግባራዊነትም የክልል ውሃ ቢሮዎች ለነበራቸውም ማቺንግ ፈንድ አድንቀው ፕሮጀክቱ በዘላቂነት አገልግሎት እንዲሰጥ የሁሉም ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

መድረኩ በነገውም ቀን የሚቀጥል ሲሆን

የለጋሽ ድርጅቶች ተወካዮች፣ የክልል ውሃ ቢሮ ኃላፊዎች፣ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች እና ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሚመለከታቸው አመራሮችና ባለሞያዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻዎች ተሳትፈዋል።

Share this Post