ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ 34ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ኬፕታውን ገብተዋል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ 34ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ኬፕታውን ገብተዋል። ነሀሴ 7/2017(ው.ኢ.ሚ) የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የአፍሪካ ህብረት 34ኛው የመሪዎች ጉባኤ ውሳኔን ተከትሎ በህብረቱ አዘጋጀነት በደቡብ አፍሪካ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ የውኃ ኢንቨስትመንት ሰሚት ( AU AIP Africa Water Investment Summit 2025) ለመሳተፍ ደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታውን ገብተዋል፡፡ ጉባኤው በዋናነት በዘላቂ ልማት ግቦች ውስጥ በ6ኛ ደረጃ የተቀመጠውን የዘርፉን የ30 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ኢንቨስትመንት ክፍተት ለመሙላት ያለመ ሲሆን በጉባኤው በርካታ የህብረቱ አባል ሀገራት መሪዎች፤ የዘርፉ ሚንስትሮች፤ የልማት አጋር ድርጅቶች፤ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት፤ የግሉ ዘርፍ ክፍለ ኢኮኖሚ ባለድርሻ አካላት እንደሚሳተፉበት ይጠበቃል፡፡ ጉባኤው በበርካታ ሁሉን አቀፍ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለቀጣይ ሦስት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን ክቡር ሚንስትሩ በተለያዩ ከፍተኛ መድረኮች ላይ ተገኝተው በዘርፉ የኢትዮጵያን ተሞክሮ፣ አበርክቶ እና አቋም የሚያንጸባርቁ ሲሆን በሌላ በኩልደግሞ ከኢትዮጵያ ጋር መልካም ግንኙነት ካላቸው ሀገራት እና የልማት አጋር ድርጅቶች ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶችን እንደሚያደርጉም ይጠበቃል፡፡

Share this Post