ከ227 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የፀሓይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ከ227 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የፀሓይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ሰኔ13/2018 ዓም (ው.ኢ.ሚ)የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በመተባበር በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ዞን ሆኮ ወረዳ ከ227 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገገበት ቦኮሆዲ የፀሀይ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ ዛሬ ያሰመረቅነው ፕሮጀክት ከ227 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት እና ከ2 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን የኤሌክትሪክ ሀይል ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው በማከል በጣም ገጠራማ አካባቢዎች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሀይል ተጠቃሚ ለማድረግ በአደሌ ፕሮጀክት ከአለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ብድር በክልሉ ለመገንባት ከታሰቡት አምስት ፕሮጀክቶች ዛሬ ያስመረቅናቸውን ጨምሮ ሁለት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ፕሮጀክቶቹ የአካባቢውን ህብረተሰብ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በመፍታት ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ይረዳል ብለዋል።

በመጨረሻም ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው የአካባቢው ማህበረሰብ ፕሮጀክቱን እንደራሱ ንብረት አድርጎ ሊጠብቅ ይገባል በማለት መልክት አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተወካይ አቶ ክንፈ ነጋሽ በበኩላቸው ተቋሙ የገጠር ቀበሌዎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ አውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በክልሉ 2 የፀሀይ ሀይል ማመንጫዎች ገንብቶ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ገልፀዋል፡፡

የአካባቢውን ማህበረሰብ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ የተገነባው ፕሮጀክት 525 ኪ.ዋ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት አቅም ያላለውና ለ20አመት አገልግሎት መስጠት የሚያስችል በመሆኑም ገልጸዋል።

የሲዳማ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኢ/ር ከበደ ጋኖሌ አካባቢው ለረጅም አመታት ከልማት ርቆ የቆየ ሲሆን መንግስታችን ባለፉት ሶስትና ሁለት አመታት ወዲህ የልማት ጥያቄያቸውን እየመለሠ መሆኑን ገልጸዋል።

ቢሮ ኃላፊው ከአካባቢው የልማት ጥያቄዎች ውስጥ መንገድ፣ውሃ፣ ጤና፣ትምህርት እና መብራት የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ሁሉንም ጥያቄዎች መመለስ ተችሏል ብለዋል።

የአካባቢውን የልማት ጥያቄያቸው የሆነውን የፕሮጀክት እውን እንዲሆን ላደረገው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በተለይም ለዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ፣ፕሮጀክቱን ጨርሰው ለሰጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አገልግሎት እና የአካባቢው ማህበረሰብን አመስግነዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ፣ባለሙያዎች ፣የሀገር ሽማግሌዎች እና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

Share this Post