ከ 20 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የጣንቋ አበርገሌ የውሃ አቅርቦት ፕሮጀክት ግንባታ ቁጥጥር ውል ስምምነት ተፈረመ::
ከ 20 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የጣንቋ አበርገሌ የውሃ አቅርቦት ፕሮጀክት ግንባታ ቁጥጥር ውል ስምምነት ተፈረመ::
ሀምሌ /2017 ዓ/ም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጣንቋ አበርገሌ ባለብዙ መንደር የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ፕሮጀክት የግንባታ ክትትል እና የማማከር ውል ስምምነት ኤሲኤ ራይዚን ኮሰልታንት ኃ.የተ.የግ.ማ. አማካሪ ድርጅት ጋር ተፈራረመ።
የግንባታ ክትትል ውሉን የፈረሙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ደ/ር አስፋው ዲንጋሞ ሲሆኑ በአማካሪ ድርጅቱ ሚኒስትር መስሪያቱን ወክሎ ጥራቱን በጠበቀ እና አካባቢው ውሃ አጠር በመሆኑ በተያዘለት ጊዜ ስራው እንዲያጠናቀቅ የማማከር ስራው እንዲሰራ አደራ ብለዋል፡፡
ኤሲኤ ራይዚን ኮሰልታንት ኃ.የተ.የግ.ማ. አማካሪ ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ ከሊፋ መሀመድ በክልሉ የተለያዩ ድርጅቶችን ሲያማክር የቆየ ድርጅት መሆኑን ገልጸው በዚህ ስራ ላይም ያላቸውን ልምድ በመጠቀም በተያዘለት ጊዜና ጥራት እንዲሰራ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የብሄራዊ ዋን ዋሽ ፕሮግራም አካል በሆነው በCR-WaSH ፕሮጀክት በ12 ወር ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ 17 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡