በጣም ገጠራማ ለሆኑ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ሀይል ከሚያቀርቡ በዘርፍ ከተሰማሩ የ16 የግል ድርጅቶች ውል የማደስና ከ13 ተጨማሪ የግል ድርጅቶች ጋር ውል የመግባት ስነስርዓት ተካሄደ ።

በጣም ገጠራማ ለሆኑ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ሀይል ከሚያቀርቡ በዘርፍ ከተሰማሩ የ16 የግል ድርጅቶች ውል የማደስና ከ13 ተጨማሪ የግል ድርጅቶች ጋር ውል የመግባት ስነስርዓት ተካሄደ። ታህሳስ 07/2018 ዓ/ም (ውኢ ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሀገር ደረጃ በጣም ገጠራማ ለሆኑ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ሀይል ተደራሽ ከሚያደርጉ በዘርፉ ከተሰማሩ የ16 የግል ድርጅቶች ውል የማደስና ከ13 ተጨማሪ የግል ድርጅቶች ጋር ውል የመግባት ስነስርዓት ተካሂዷል ።   መርሃግብሩን በንግግር የከፈቱት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ ኢትዮጵያ እምቅ የኢነርጂ ሀብት ያላት ሀገር እንደሆነና ከለውጡ ወዲህ እንደሀገር በዘርፉ ከፍተኛ ስራ ተሰርቶ ውጤት ምጣቱን ገልፀው ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ሙሉ በሙሉ ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብና ቅንጅታዊ አሰራርን ይጠይቃል ብለዋል።   ዶ/ር ሱልጣን አክለው መንግስት በጣም በገጠራማ አካባቢ ያለውን የህብረተሰብ ክፍል የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ለዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ ከፍተኛ ስራ እየሰራ ቢሆንም የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ወሳኝና አመርቂ ውጤት ለማምጣት የሚያስችል በመሆኑ ውል ገብቶ ወደ ስራ ማስገባት አስፈልጓል ብለዋል።   በ2030 የኢትዮጵያ እያንዳንዱ ሰፈር የኤሌክትሪክ ሀይል ተጠቃሚ እንደሚሆን በሃገር ደረጃ የታቀደ መሆኑን ያወሱት ሚኒስትር ድኤታ ዕቅዱን ተግባራዊና ውጤታማ ለማድረግ ውል የሚያድሱም ይሁን አዲስ ውል የሚፈርሙ የግሉ ዘርፍ በከፍተኛ ሀላፊነትና በሀገር ፍቅር ስሜት ህብረተሰቡን ከጨለማና ከኋላቀርነት የማላቀቅ ስራ መስራት አለባቸው ብለዋል።   በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴ የአዴሌ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ አዲስአለም መብራቱ በበኩላቸው በፕሮጀክቱ እስካሁን ታቅደው የተከናወኑ ስራዎች የመጡ ውጤቶችና አጠቃላይ ገጽታው ምን እንደሚመስል አጭር ሰነድ አቅርበው ተሳታፊዎች ጥያቄና የተለያዩ ሀሳቦች አንስተው ዶ/ር ሱልጣን ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።   በመርሃግብሩ ላይ በዘርፉ የተሰማሩና ውል የገቡ የግል ድርጅቶ፣ የክልሎች የኢነርጂ ዘርፍ ሀላፊዎችና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የዘርፉ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል ።

Share this Post