ከ 135 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የሆቢቻ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ከ 135 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የሆቢቻ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። ​ግንቦት 2/2018 ዓ.ም | ወላይታ ዞን በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ስር በሚመራው "የሆርን አፍሪካ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት" አካል የሆነው እና ከ135 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተገነባው የሆቢቻ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት በቅቷል። በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ​የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ ተገኝተው ፕሮጀክቱን ያስጀመሩ ሲሆን ፕሮጀክቱ በዋናነት ባለፉት ስምንት አመታት መንግሰት ባካሄደው ሪፎርም ፕሮጀክት ጀምሮ በማጠናቀቅ ለውጥ ያመጣ ሰው ተኮር ፓርቲ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል። በሆቢቻ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ለ5ቀበሌ ውሃ እንዲጠጡ ማድረግ ለህብረተሰቡ እርካታ ለሰራው ደግሞ ትልቅ ስኬት ነውም ብለዋል። ይህ ስራ በወረዳው ለዘመናት የነበረውን የንፁህ መጠጥ ውሃ እጥረት በዘላቂነት እንደሚፈታም ርእሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። ክቡር አቶ ጥላሁን በማከል የክልሉን የመጠጥ ውሃ ሽፋን ለማሳደግ ከክልሉ መንግስት ጎን ሆኖ እየደገፈን ላለው ለዜጎች ብልፅግና እየሰሩ ያሉትን የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ እንዲሁም ክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞን ኮንትራክተርና አማካሪውን ከልብ አመሠግናለሁ ብለዋል። በመጨረሻም ፕሮጀክቱን የሚያስተዳድሩት የስራ ሃላፊዎች በፍትሀዊነት እንዲያስተዳድሩ ማህበረሰቡም ይህንን ትልቅ ፕሮጀክት እንደ ንብረቱ እንዲያየውና በጥንቃቄ እንዲጠብቀው ጥሪ አቅርበዋል በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ በዚህ ፕሮጀክት መጠናቀቅ በሺዎች የሚቆጠሩ የሆቢቻ ወረዳና የአካባቢው ቀበሌ ነዋሪዎች ንፁህ ውሃ ማግኘት መጀመራቸውን ገልጸዋል። የሆቢቻ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ዉሃ ፕሮጀክት አካል መሆኑን ገልጸው ለዚህ ስራ ከ135ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበትና ከ31ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረጉን ጨምረው ገልጸዋል። ፕሮጀክቱን አጠናቀን ለህብረተሰቡ ስናስረክብ ህብረተሰቡ መንከባከብ ብቻ ሳይሆን የውሃ አገልግሎቱ በሚዘረጋው የክፍያ ስርአት መሠረት በመክፈል ብክነትን በመቀነስ ውሀውን በቁጠባ መጠቀም ይገባልም ሲሉ አሳስበዋል። ​ለፕሮጀክቱ ስኬት ከፍተኛ በጀት የተመደበ ሲሆን ለህብረተሰቡ ጤና፣​ለሴቶችናህጻናት፣ ለትምህርት ብሎም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ለማቅለል ጠቀሜታው የጎላ ነው። በመርሀግብሩ ላይ የክልሉ ርእሰ መስተዳድርን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች የሀገር ሽማግሌዎች እና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

Share this Post