የፕሮጀክት አስተዳደር ጋይድላይንና የአውታር መጽሔት ቁጥር ሁለት ለግምገማ ቀረቡ።
አዳማ: መስከረም 19/2019ዓ.ም
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የፕሮጀክት አስተዳደር ጋይድላይንና የ"አውታር" መጽሔት ቁጥር ሁለትን ለግምገማ አቀረበ።
ጋይድላይኑ የፕሮጀክቶችን የተሳካ አፈጻጸም፣ የተደራጀ አስተዳደር፣ ውጤታማ ርክክብና ዘላቂነት ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንዳለው የሚኒስቴሩ የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኦልቀባ ባሼ ገለጹ።
አቶ ኦልቀባ ይህን የገለጹት የሚኒስቴሩ ሥራ አስፈጻሚዎች ሰነዶቹን ለመገምገም በተዘጋጀ መድረክ ላይ ነው።
ፕሮጀክቶች የሕዝብን የውሃና የኢነርጂ ፍላጎት ከማሟላትና የአገሪቱን የልማት ግቦች ከማሳካት አንጻር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳላቸው የጠቀሱት አቶ ኦልቀባ፣ ከዕቅድና አፈጻጸም ጀምሮ እስከ ማጠናቀቂያ፣ ርክክብና ድህረ-ግንባታ ድረስ በተቀናጀ ሥርዓት መመራት እንደሚገባ አስረድተዋል።
የፕሮጀክት አስተዳደር ጋይድላይኑ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ፣ በተመደበላቸው በጀትና በተፈለገው የጥራት ደረጃ እንዲፈጸሙ የሚያግዝ ሲሆን፣ ፕሮጀክቶች በተገቢው ሁኔታ ተጠናቀው ለሚመለከታቸው አካላት እንዲረከቡ ያስችላል። የተገነቡ ፕሮጀክቶችም በዘላቂነት አገልግሎት እንዲሰጡና በአግባቡ እንዲጠበቁ አቅጣጫ ይሰጣል ብለዋል።
ጋይድ ላይኑ ከተቋሙ የሥራ ሁኔታና ከተግባራዊ ተሞክሮዎች ጋር ያለውን ተዛምዶ በመመርመር፣ ክፍተቶችን በመለየትና ግብዓቶችን በማሰባሰብ ማሻሻያዎችን ማካተት እንደሚገባ አቶ ኦልቀባ ገልጸዋል።
ጋይድ ላይኑ በኮሚቴ የተዘጋጀሲሆን፣ የተሳታፊዎች የሙያ እውቀትና ተሞክሮ ለጥራታቸውና ለተግባራዊነታቸው ወሳኝ መሆኑንም አክለዋል።
በሌላ በኩል ለግምገማ የቀረበው የ"አውታር" መጽሔት ቁጥር ሁለት የሚኒስቴሩን የሥራ አፈጻጸም፣ በውሃና ኢነርጂ ዘርፎች የተከናወኑ አንኳር ተግባራትን፣ የተመዘገቡ ውጤቶችን፣ የተቋማዊ ለውጥና የዲጂታላይዜሽን ሥራዎችን እንዲሁም የተሞክሮ ልውውጦችን የሚዳስስ ሲሆን፣ የተቋሙን የአምስት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ውጤቶችም አካቷል።
በመጽሔቱ ግምገማ የይዘቱን ተገቢነት፣ የመረጃዎችን ትክክለኛነትና የአቀራረብ ጥራት በመመርመር፣ የተቋሙን ውጤታማ አፈጻጸም በተገቢው ሁኔታ እንዲያንጸባርቅ የሚያስፈልጉ ማሻሻያዎች ላይ ውይይት ተደርጓል።
የአውታር መጽሔት የሚኒስቴሩን የሥራ ውጤቶችና የለውጥ ጉዞ ለማስተዋወቅ፣ የተሳኩ ተሞክሮዎችን ለማጋራትና ተቋማዊ የእውቀት ልውውጥን ለማጠናከር የሚያግዝ መሆኑን አቶ ኦልቀባ አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።
የፕሮጀክት አስተዳደር ጋይድ ላይኑን ረቂቅ ዶ/ር አደማሱ ቴሶ በስፋት አብራርተው ያቀረቡ ሲሆን የአውታር መጽሔት ረቂቁን ደግሞ አቶ ቴዎድሮስ መርጊያ ለውይይት መነሻነት አቅርበዋል።
በቀረቡ ሰነዶች ላይ ሰፊ ውይይት የተደሰገ ሲሆን በነገው እለትም በሚቀርቡ ሰነዶች ውይይቶች የሚቀጥሉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto