የድርቅ ስጋትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ቴክኒካል የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።

የድርቅ ስጋትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ቴክኒካል የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ። መስከረም 05/2019 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደርን ዕውን ለማድረግ ከሚያግዙ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ በሆነው በባዘርኔት ፕሮጀክት የድርቅ ስጋትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ቴክኒካል የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ። የስልጠናውን መርሃግብር ያስጀመሩት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የባዘርኔት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሞላ ረዳ እንደውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የድርቅ ክስተትን በመረዳት እንዴት መከታተል እንደሚቻልና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራዎች ላይ ምን መሰራት እንዳለበት ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያለመ ስልጠና ነው ብለዋል። ስልጠናው የድርቅ ስጋትን መረዳት፣ ስጋቱንና ተፅዕኖውን መገምገም፣ ድርቅን መከታተል እና ቅድመ ማስጠንቀቂያን ወደ ቅድመ እርምጃ መቀየር ላይ ያተኮራል ያሉት አቶ ሞላ ስልጠናው ተቋሙ ከCIMA ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመው፤ ሰልጣኞች በየቤዚኑ ያለውን ተሞክሮዎችንም እንዲያጋሩ እና ስልጠናውን በአግባቡ እንዲከታተሉ አሳስበዋል። ከሚኒስቴር መ/ቤቱ፣ ከአዋሽና ከዋቢሸበሌ ቤዚን እና ከኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ስልጠናው ላይ ተሳትፈዋል። ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ፌስቡክ https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/ ቴሌግራም http://t.me/mowieethiopia ዌብሳይት http://mowe.gov.et X/ትዊተር https://x.com/mowe_ethiopia ዩቱዩብ https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s ቲክቶክ tiktok.com/@mowetikto

Share this Post