ኢትዮጵያ አሸንፋለች!
ኢትዮጵያ አሸንፋለች! 🇪🇹 ነሐሴ/16/2018 (ው.ኢ.ሚ) ዛሬ ኢትዮጵያ ታሪካዊ ድል አስመዝግባለች። ለዘመናት ተሞክረው ሳይሳኩ የቆዩ የሀገራዊ ምክክር ጥረቶች በውጤታማ ሂደት ተጠናቀው፣ ሀገራዊ መግባባትን ለማጠናከር አዲስ ተስፋ ተፈጥሯል። ከአርሶ አደሩ እስከ አርብቶ አደሩ፣ ከሀይማኖት አባቶች እስከ ምሁራን፣ ከወጣቶችና ሴቶች እስከ ተወካዮች የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በሂደቱ ተሳትፈዋል። የተለያዩ አመለካከቶች፣ ልምዶችና ስጋቶች በአንድ የምክክር መድረክ ተደምጠዋል። ይህ ስኬት የአንድ ወገን ድል ሳይሆን የኢትዮጵያ ድል ነው። የአንድ ቡድን ድል ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያውያን ድል ነው። ምክክር ማለት ልዩነቶችን በግጭት ሳይሆን በውይይት፣ በመደማመጥና በመግባባት ለመፍታት የሚያስችል የሰላም መንገድ ነው። ዛሬ የተገኘው ውጤት የመጨረሻ መዳረሻ ሳይሆን የአዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ ነው። የምክክሩ ውጤቶች በተግባር እንዲወርዱ፣ በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች እንዲተገበሩና የሁሉም ዜጎች የጋራ ተሳትፎ እንዲጠናከር ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት ይጠይቃል። በመደማመጥ የሚገነባ መግባባት፣ በመግባባት የሚጸና ሰላም፣ በሰላም ላይ የሚገነባ ልማትና ብልፅግና—ይህ የኢትዮጵያ የወደፊት ጉዞ መሠረት ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ አሸንፋለች! የጋራ ድምፅ አሸንፏል! ምክክር አሸንፏል! ሰላምና መግባባት አሸንፈዋል! ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!