ፕሮጀክቱ በመብራት እጦት ምክንያት ሲደርስብን የነበረውን እንግልት የቀነሰ ነው

ፕሮጀክቱ በመብራት እጦት ምክንያት ሲደርስብን የነበረውን እንግልት የቀነሰ ነው

*******************

የሀሪሮ ቀበሌ ነዋሪዎች

ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በጋራ ምስራቅ ሀረርጌ ዞን ቁንቢ ወረዳ ሀሪሮ ቀበሌ 600 ኪሎ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የምርቃት ስነስርዓት ላይ በመብራት እጦት ምክንያት ይደርስ የነበረውን እንግልት እንደቀነሰላቸው ነዋሪዎች ገለፁ።

የቁምቢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ሸረፋ ወረዳው ሰፊ የቆዳ ስፋት ያለው በመሆኑ ከፍተኛ የኃይል ፍላጎት እንደነበረ አስታውሰው፤ በቀጣይ ተደራሽ ያልሆኑ ቀበሌዎችን የኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

የሀሪሮ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳልካቸው ሀውልቴ በበኩላቸው ነዋሪዎቹ የ24 ሰዓት የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ በመሆናቸው ከማህበራዊ አገልግሎት ተቋማት በቂ አገልግሎት ማግኘት ተችሏል፤ በቀጣይም ወጣቶችን በማደራጀት የስራ ፈጠራ ላይ ለማሰማራት መታቀዱን ነው የጠቆሙት።

በቀበሌው የኢንስታሌሽን እና የቆጣሪ ስፖንሰር የተደረገ ነው ያሉት አቶ እንዳልካቸው ህብረተሰቡ እንደግል ንብረት እንዲጠብቁና የአገልግሎት ክፍያቸውን በአግባቡ እንዲከፍሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እንደተሰራም አክለዋል።

የሀሪሮ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የነርሶች ኃላፊ አሸብር ወንድሙ ከዚህ በፊት በመብራት ችግር እንደህክምና ተቋም መሰጠት የነበረበትን አገልግሎት ለመስጠት ሲቸገሩ እንደነበር አስታውሰው፤ አሁን እንደአስፈላጊነቱ ሁሉንም በሚባል ደረጃ ቀልጣፋና በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት መስጠት ችለናል ብለዋል።

በመብራት እጦት ምክንያት ይደርስ የነበረውን እንግልት የቀነሰ ፕሮጀክት ነው ያሉት የሀሪሮ ቀበሌ ነዋሪዎች አቶ ሻሚል አደምና ወ/ሮ ሂክማ ቀመር በበኩላቸው ተማሪዎችም በኩራዝ ሲያጠኑ እንደነበር፣ በማገዶ ሲያበስሉ እንደነበርና እናቶች በወሊድ ሰዓትም ሆስፒታል ለመውለድ ሲቸገሩ እንደነበር ነው የጠቆሙት።

ፕሮጀክቱ ዘመናዊ ማብሰያዎችንም በመጠቀም ኑሯቸውን ስላቀለላቸው ሚኒሰቴር መስሪያቤቱንና ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን አስተዋጽኦ ያበረከቱትን ሁሉ አመስግነዋል።

ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ

https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/

ቴሌግራም

http://t.me/mowieethiopia

ዌብሳይት

http://mowe.gov.et

X/ትዊተር

https://x.com/mowe_ethiopia

ዩቱዩብ

https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s

ቲክቶክ

tiktok.com/@mowetikto

Share this Post