ፕሮጀክቱ የጤናና ማህበራዊ ችግራቸውን እንደሚፈታላቸው ገለጹ።

ፕሮጀክቱ የጤናና ማህበራዊ ችግራቸውን እንደሚፈታላቸው ገለጹ። ታህሳስ9/2018 (ው.ኢ.ሚ)የውሀና ኢነርጅ ሚኒስቴር በቦረና ዞን መዳ ወላቡ ወረዳ ለቢዲሬ ከተማና አካባቢው ያስገነባው የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ለዘመናት የቆዬ ችግሮቻቸውን እንደሚፈታላቸው አካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።   የአባ ሶርባ ቀበሌ ነዋሪ ወ/ሮ አይሻ ማልሞ ከድር እንደገለጹት ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የውሀ ችግር እንደነበርና አሁን ላይ የዚህ ፕሮጀክት መተግበር የመጠጥ ውሃ ፍላጎትን ብቻ ሳይሆ ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ እና ከጤና ጋር ተያያዠ የሆኑ ችግሮችን እንደሚፈታላቸው ገልጸዋል።   ወ/ሮ አይሻ ፕሮጀክቱ በተለይ ለሴቶች ውሃ ለመቅዳት የሚያባክኑትን ጊዜና በሸክም ምክኒያት የሚደርስባቸውን ከፍተኛ የጤና ችግር ሙሉ በሙሉ በማስቀረት ጤናማ ማህበረሰብ በመፍጠር በውሃ ብክለት የሚፈጠረውን ህመምና ሞት የሚያስቀር ልጆችን ወደ ትምህርት ገበታቸው የሚመልስ መሆኑን በመግለጽ በፕሮጀክቱ ትግበራ የተሳተፉትን አካላትን አመስግነዋል።   ሌላኛዋ የንጹህ መጠጥ ውሀ ተጠቃሚ የሆነችው ወ/ሮ አይሻ ኢብራሂም በፕሮጀክቱ የተሰማትን ደስታ በመግለጽ እስከዛሬ ከፍተኛ የሆነ የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር የነበረባትና ውሃ ለመቅዳት ስታጠፋ በነበረው ሰአት ልጆቿ ከትምርት ይቀሩና ይራቡ እንደነበር፣ነፍሰ ጡር ሴቶች ሳይቀሩ ወንዝ ላይ የወለዱበት አጋጣሚ እንደነበር ገልጻ አሁን ላይ ይሄ ሁሉ ችግር ተፈቶ በማየቷ መንግስትን እና ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ያደረጉ አካላትን አመስግናለች።   ወ/ሮ አይሻ በማከል ፕሮጀክቱ ከመጠጥ ውሃ ባለፈ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚሰጥና በተለይ ለትምህር ቤቶች ፣ ለጤና ተቋማት እንዲሁም የአካባቢው እድገት ልማቱ እንዲፋጠን ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በአግባቡ ለሁሉም ህብረተሰብ መዳረስ እንዲችልና የውሃ ብክነት እንዳይፈጠር በፍትሀዊነት መጠቀም ፕሮጀክቱን ለመጠበቅ የከተማው ውሃ አገልግሎት እና ህብረተሰቡ በጋራ መስራት ይጠበቅበታል በማለት አስተያየትም ሰጥተዋል።   ፕሮጀክቱ ሶስት የውሃ ማጠራቀሚያ ሪዘርቫየር ያለውና ሶላር ፓምፕ የተገጠመለት ከ36 ሺ በላይ ቢድሬ ከተማ ነዋሪዎችና 3 የሳተላይት መንደሮች ተጠቃሚ የሚያደርግና ከዩኒሴፍ (KfW)፡የገንዘብ ምንጭ 4.16 ሚሊዮን ዶላር ከመንግሥት 1.23 ሚሊዮን ዶላር ባጠቃላይ ከ5.38 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባና ለ25አመት እንዲያገለግል ታሳቢ ያደረገ ነው።

Share this Post