በዘርፉ የተመዘገበውን ለውጥ ለማስቀጠል ከአጋር አካላት ጋር በጋራ መስራት የጎላ ሚና አለው።

በዘርፉ የተመዘገበውን ለውጥ ለማስቀጠል ከአጋር አካላት ጋር በጋራ መስራት የጎላ ሚና አለው። ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር Mr. Sune Krogstrup ጋር በከርሰምድር ውሃ ካርታ (ground water mapping) እና በአቅም ግንባታው ዘርፍ በትብብር ለመስራት በሚያስችል ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።   ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ በውይይታቸው ወቅት የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል ቴክኖሎጂዎችን በውሃው ዘርፍ ላይ ተግባራዊ ለማድረግ በከርሰምድር ውሃ ፍለጋና ጥናት በጂኦሳይንስና በሃይድሮሎጅ ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።   በተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ የተመዘገበውን ለውጥ ለማስቀጠል ከአጋር አካላት ጋር በጋራ መስራት የጎላ ሚና አለው ብለዋል ክቡር ሚኒስትሩ። የዴንማርክ አምባሳደር Mr. Sune Krogstrup በበኩላቸው በከርሰምድር ውሃ ካርታ ዙሪያ ዘመናዊ የጂኦፊዚካል ቴክኖሎጂዎችን በውሃው ዘርፍ ላይ ተግባራዊ ለማድረግ ከዩኒቨርስቲዎች ጋር በጋራ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ላይ እንሰራለን ብለዋል።   የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከዴንማርክ መንግስት ጋር በመተባበር በ5 አመታት የሚተገበር የፈጣን የከርሰምድር ውሃ ሀብት ፍለጋና ጥናት ካርታ በኢትዮጵያ የውሃ ዘርፍ ላይ ተግበራዊ ለማድረግ ባለፈው አመት ይፋ የተደረገ ፕሮጀክት በመሆኑ በቀጣይም ከተቋሙ ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ተወያይተዋል።

Share this Post