የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ከውሀ ሀብት እና ከመስኖ ልማት ሚኒስቴር የመጡ ልኡካን በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እየተተገበሩ ያሉ ስራዎችን ጎበኙ።

የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ከውሀ ሀብት እና ከመስኖ ልማት ሚኒስቴር የመጡ ልኡካን በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እየተተገበሩ ያሉ ስራዎችን ጎበኙ። ታህሳስ4/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ የውሀ ሀብት እና የመስኖ ልማት ሚኒስቴር የመጡ ልኡካንን የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ተቋም የሆነውን የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩት ፣የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የአቃቂ ፍሳሽ ማጣሪያ ማእከልንና የአዳማ ከተማ ውሃ አገልግሎትን ጎብኘተዋል።   ሉኡካን ቡድኑ በተለይ የውሃ ቴክኖሎጂ ስልጠና እና ማማከር ማእከል እየሰጣቸው ባሉ የውሃ ቴክኖሎጂ ስልጠና እና ማማከር ምርምር እና ማማከር ፣የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማማከር፣ የውሃ ተቋማት የቴክኒክ ድጋፍ፣ልዩ ልዩ የላቦራቶሪ አገልግሎት እና ማማከር ስልጠና እና የልምድ ልውውጥ ፕሮግራሞች ላይ ከተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ታመነ ኃይሉ ጋር ተወያይተዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ በአዳማ ከተማ ውሃ አገልግሎት አቶ አህመድ ጋር የተወያዩ ሲሆን በከተማዋ አስተዳደር የክልሉን ባህልናወግ የሚገልጽ ስጦታም ተበርክቶላቸዋል ።   ሉኡካን ቡድኑ ለተደረገላቸው አቀባበል በማመስገን የልምድ ልውውጡ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ቤተሰባዊ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠነክር መሆኑን ገልጸው በተለይ በዉሃ ላይ ያለው አሰራርና አስተዳደር ጥሩ ልምድ ማግኘታቸውን ገልጸዋል። ሉኡካኑ በቀጣይ አራት ቀናትም ያልታዩ ዘርፎችን እንደሚያዩና ውይይቶችም እንደሚኖራቸው ከአስተባባሪዎቹ ተረድተናል።

Share this Post