ሀገራችን ያላትን የውሃ ሀብት እንድናውቅ የሚደረገው ጥረት በትምህርት ሊደገፍ ይገባል ሲሉ ተማሪዎች ገለጹ፡፡
ህዳር 24/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የቪዥን አካዳሚ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዲጂታል ኤግዚቢሽኑን በጎበኙበት ወቅት ሀገራችን ያላትን የውሃ ሀብት እንድናውቅ የሚደረገው ጥረት በትምህርት ሊደገፍ ይገባል ሲሉ ተማሪዎች ገለጹ፡፡
የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው መሬም አብዱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትልቅ ስራ እየሰራ መሆኑን መረዳቷን ገልጻ በተለይ ውሃ፣አየር እና የጸሀይ ሀይልን ተጠቅሞ የኤሌክትሪክ ሀይል እያመነጨ እንደሆነ፤ በውሃ ማጣራት ላይ ያየሁት የውሃ ማጣራት ስራ በጣም አስፈላጊ እና የውሃ ብክለትንና ቁጠባን ያዘመደ በመሁኑ ሊበረታታና ሁሉም ሊጠቀምበት ይገባል በመሆኑም ሀገራችን ያላትን የውሃ ሀብት እንድናውቅ የሚደረገው ጥረት በትምህርት ሊደገፍ ይገባልም በማለት አስተያየቷን ገልጻለች፡፡
በጉብኝቱ ላይ ብዙ ነገሮች ተምሬያለሁ የሀገሬ ያላትን የውሃ ሀብት ምን ያህል እንደሆነ ና እኛም የራሳችን የሆነውን ነገር ማወቅ መጠበቅ እንዳለብን የተረዳሁበት በተለይ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያለበትንና ለኢትዮጵያ የሚያመጣውን የኢኮኖሚ እድገት እንዲሁም በውሃና የኢነርጂ ሀብት ምን ይመስላል የሚለውን ያየሁበት ጉብኝት ነው ያለን ደግሞ የ7ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ቅዱስ ዜና ነው፡፡
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ተማሪዎች በዚህ ልክ መጥተው ሀገራቸው ያላትን የውሃና ኢነርጂ ሀብት እንዲረዱ ማድረጉ ሊመሰገንና ሊበረታታ እንዲሁም ሌሎች ተቋማት ሊወስዱት የሚገባ ተሞክሮ ጭምር መሆኑንም መምህራኖች ገልጸዋል፡፡