በኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ልማትፕሮጀክት የሩብ ዓመት የግምገማ ሪፖርት ቀረበ፡፡
ህዳር16/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት የሩብ ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርት ቀረበ፡፡
መርሀ ግብሩን የከፈቱት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ናቸው፡፡
ክቡር አምባሳደር በኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ለማት ፕሮጀክት በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች በተደጋጋሚ ከሚጠቁ አምስት የአፍሪካ አገራት የመጠጥ ውሃ እና መስኖ ልማት ዋነኛ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ አካባቢያዊ እና ማህበራዊ የልማት አገልገሎቶች ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታውሰዋል፡፡
በኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት ክትትልና ግምገማ ከፍተኛ ባለሞያ አቶ ሀብታሙ አየለ የፕሮጀክቱን ጅማሮ፣በፕሮጀክቱ ትኩረት የተደረገባቸው አካባቢዎች፣የፋይናንስና የግዢ አስተዳደራዊ ጉዳዮች፣ማህበረሰባዊ ተጽዕኖዎች፣ የገጠሙ ተግዳሮቶችና የተወሰዱ መፍትሄዎች እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮችን ያካተተ የግምገማ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
ሪፖርቱን አስመልክቶ ተሳታፊዎቹ ገንቢ ሃሳብና አስተያየቶችን የሰነዘሩ ሲሆን አብዛኞቹን ፕሮጀክቶች የሚገጥሟቸው የግምገማ ሂደት መዘግየት፣የግዢና የኮንትራት አስተዳዳደር ስራዎች መጓተት፣የዲዛይን ጥናት ጉድለት፣የአማካሪዎች በወቅቱ ምላሽ አለመስጠትና የኮንትራክተሮች ክፍተት በዚሁ ፕሮጀክት ላይ እንዳይገጥሙ በሚገባ በማጤን በወቅቱ ማጠናቀቅ ስለሚገባ ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ግምገማው በቢሮና በመስክ ለተከታታይ አስር ቀናት የሚካሄድ ሲሆን በሂደቱ የሚኖሩ ግኝቶችን እንደግብዓት በመውሰድ ማሻሻያዎች እንደሚኖሩም ይጠበቃል ተብሏል፡፡
በሚኒስቴር ዴኤታ ማዕረግ የክቡር ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳ፣ከአለም ባንክ የተውጣጡ ልዑካን ፣የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች፣አማካሪዎችና ሌሎች አስፈጻሚዎች በግምገማ ሪፖርቱ ላይ ተሳትፈዋል፡፡