በሁለተኛው ዙር የመንግስት አገልግሎት አስተዳደር ሪፎርም ላይ ውይይት ተደረገ።

በሁለተኛው ዙር የመንግስት አገልግሎት አስተዳደር ሪፎርም ላይ ውይይት ተደረገ። ነሀሴ 12/2017ዓም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በሁለተኛው ዙር የመንግስት አገልግሎት አስተዳደር ሪፎርም ላይ ተወያይተዋል ። በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የመጀመሪያው ዙር የመንግስት የአገልግሎት ሪፎርም ከአራት አመት በፊት ተግባራዊ መደረጉን አውስተው በአተገባበሩ የቀሩ ነገሮችን መለየትና እና ምን እየሰራን ነው የሚለውን መፈተሽ ይገባል ብለዋል። ሁለተኛው ዙር የመንግስት አገልግሎት አስተዳደር ሪፎርም ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ አንደ ሀገር የሲቪል ሰርቫንቱ ዋና ተግባር አገልጋይነት በመሆኑ ተቋማዊ አቋምን በማስተካከልእና በመገንባት ረገድ ባሳለፍናቸው አራት አመታት በርካታ ስራዎችን ሰርተናል፤ የቀሩት ላይ ደግሞ በቀጣይ የምንሄድባቸው ይሆናል ብለዋል ። አንድ አመራር እንደ ንስር የመንግስትን አቅጣጫ ከፍ ብሎ በማየት ዝቅ ብሎ ደግሞ ከታችኛው አመራር አንቀሳቃሽ ሀይል ጋር በመስራት የተሻለ ተቋም መፍጠር ይገባልም ብለዋል። የሁለተኛው ዙር የመንግስት አገልግሎት አስተዳደር ሪፎርም ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ሰነድን ያቀረቡት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ሃይሌ ናቸው። ሰነዱ ሪፎርም ለማድረግ የፖሊሲው መነሻዎች፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ እርካታ አለመኖር፣የተቋማት አደረጃጀት፣ የሙያ ምድብ፣ የስራ ምዘናና የክፍያ ስርዓት አለመኖር፣ብቁየሰው ኃይል እጥረትና የበቁ የሲቪል ሰርቪስ ተቋማት ያለመኖር፣ የሲቪል ሰርቪሱ ገለልተኝነት፣ ለፖሊሲ ውሳኔ አጋዥ የሆነና የተደራጀ የተሟላ የሰው ሃይል መረጃ አያያዝ አለመዳበር ላይ ያሉትን ክፍተቶች በዝርዝር ይዟል። ኮሚሽነሩ ሁለተኛው ዙር የመንግስት አገልግሎት አስተዳደር ሪፎርም እንደ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ቀልጣፋና ተደራሽ የመንግስት አገልግሎት አቅርቦት ስርዓትን ለመዘርጋት ፣የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ፣ የቅሬታና አቤቱታ ስርዓት፣ አገልግሎቶችን ለሶስተኛ ወገን የማሻገር አሰራር፣ የሙያ ምድብ ደረጃና የስራ ምዘናን ውጤት ተኮር እንዲሁም ሌሎች ስራዎች ላይ በመስራት ለሪፎርሙ ተግባራዊነት መዘጋጀት አለበት ብለዋል። በመጨረሻም በሪፎርሙ ላይ ከሚኒስትሪው አደረጃጀት በመነሳት ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ክቡር ሚኒስትሩ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

Share this Post