በውሃው ዘርፍ ላይ የሚታየውን የኢንቨስትመንት ክፍተት ለመሙላት መንግስታት ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት፣ ተስማሚ ፖሊሲ ማዘጋጀት እና ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር እንደሚገባቸው ተገለፀ ።
ነሀሴ 9/2017ዓም(ውኢሚ)የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በድቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ከተማ ሦስተኛ ቀኑን በያዘው የአፍሪካ የውኃ ኢንቨስትመንት ሰሚት ( AU AIP Africa Water Investment Summit 2025) የማጠቃለያ ዋና መድረክ ላይ በፓናሊስትነት በነበራቸው ተሳትፎ የኢትዮጵያን ተሞክሮ አካፍለዋል::
ክቡር ሚንስትሩ በውሃው ዘርፍ የሚታየውን የኢንቨስትመንት ክፍተት ለመሙላት እና የአፍሪካን ሕዝብ ጥያቄ ለመመለስ በዋነኝነት የመንግስታት ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ፣ተስማሚ ፖሊሲ ማዘጋጀት እና ለግሉ ዘርፍ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር እንደሚገባ ለጉባኤው ገልፀዋል ።
በዚሁ የማጠቃለያ ዓብይ መድረክ ላይ በመንግሥታት በኩል ለዘርፉ የሚመደበውን በጀት በማሳደግ እና አሳሪ ቢሮክራሲዎችን በማስወገድ የግሉን ዘርፍ ክፍለ ኢኮኖሚ ተሳትፎ ማነቃቃት እንደሚቻልም ክቡር ሚንስትሩ አስረድተዋል::
አያይዘውም ኢትዮጵያ Children's Investment Fund Foundation (CIFF) ከተባለ ግለሰባዊ ፊላን ትሮፒ ጋር የጀመረችውን በጎ የሁለትዮሽ የልማት ትብብር እንደማሳያ አቅርበዋል::
ለውሃ የምንሰጠውን ማህበራዊ ዋጋ ያህል ኢኮኖሚያዊ ዋጋ በመስጠት ተጠቃሚውን ማህበረሰብ ተገቢውን ከፍያ ማስከፈል በተግባር ሊገለጥ ይገባል ያሉት ክቡር ሚንስትሩ መሰረታዊ የአስተሳሰብና የአተያይ ለውጥ በማምጣት የግሉ ዘርፍ አዋጭነቱን እንዲረዳ መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል::