አቅመ ደካሞችን መደገፍ በልምምድ የመጣ ሳይሆን ባህላችን ነው ሲሉ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ገለጹ።

አቅመ ደካሞችን መደገፍ በልምምድ የመጣ ሳይሆን ባህላችን ነው ሲሉ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ገለጹ። ሀምሌ22/2017ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የተመራው ቡድን በአፋር ክልል ገቢ ረሱ ዞን አሚባራ ወረዳ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር አቅመ ደካሞችን መደገፍ በልምምድ የመጣ ሳይሆን ነባር ባህላችን ሲሉ ክቡር ሚኒስትሩ ገልጸዋል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ለሀገራችን ትልቅ አስተዋጾ ላበረከቱ አቅመ ደካሞች 16ቤቶችን ሰርተን እናስረክባለን ብለዋል። በተመሣሣይ በዞኑ ለሚገኙ የነገ ሀገር ተረካቢ አንድ ሺ ተማሪዎች ለትምህርት ቁሳቁስ የሚሆናቸውን ደብተርና እስክርቢቶ ድጋፍ በማድረግ ነጋችን ዛሬ እንሰራለን ብለዋል። ለዚህ ፕሮግራም እገዛ ያደረጉላቸውን የኢትዮጵያ ውሃ ስራዎች ኮንትራክተሮችንና ተጠሪ ተቋማትን አመስግነዋል። የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የክልሉ ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ እና የፕላን ቢሮ ሀላፊ ክቡር አሊ መሀመድ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሚገነቡት 16 የአቅመ ደካሞች ቤት ርክክብ ላይ በመገኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በክልሉ የተለያዩ ስራዎችን መስራቱ የነበረንን የመረዳዳት፣ የመደጋገፍ እሴታችን ማሳያ ነው ብለዋል። በመርሀ ግብሩ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ፣የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች የተጠሪ ተቋማት አመራሮች እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ ተሳትፈዋል።

Share this Post