የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራቸውን በአፋር ብሔራዊ ክልል ገቢ ረሱ ዞን አሚባራ ወረዳ አስቀመጡ።

"በመትከል ማንሰራራት" የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራቸውን በአፋር ብሔራዊ ክልል ገቢ ረሱ ዞን አሚባራ ወረዳ አስቀመጡ። ሀምሌ22/2017ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን ''በመትከል ማንሰራራት'' በሚል መርህ በአንድ ጀምበር በአገር አቀፍ ደረጃ 700 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ዘመቻን እውን ለማድረግ በአፋር ብሔራዊ ክልል ገቢ ረሱ ዞን አሚባራ ወረዳ በመገኘት አሻራቸውን አስቀምጠዋል ። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ከአራት አመት በፊት በጎንደር የጀመረ መሆኑንና በሞጆ፣በቢሾፍቱ እና በጋምቤላ ዛሬ ደግሞ በአፋር አሻራውን እያስቀመጠ መሆኑን ገልጸዋል ። የአረንጓዴ አሻራ ስራን ስንሰራ ነገን በመገንባት ለትውልድ የተሻለ ለአካባቢን ለማስረከብ ፣ የምግብ ዋስትን በማረጋገጥ የውጭ ምንዛሬን ለማሳደግ ልምምድ የሚደረግበት አመት ንደሆነ ገልጸዋል። በመርሃ ግብራችን ለሀገራችን ትልቅ አስተዋጾ ላበረከቱ አቅመ ደካሞች 16ቤት የምንሰራ እና ነገን ለሚረከቡ የወረዳው አንድ ሺ ተማሪዎች ደግሞ የትምህርት ቁሳቁስ ደብተርና እስክርቢቶ ድጋፍ እንደሚደረግና ከ10ሺ በላይ ችግኞች መተከላቸውን ገልጸው ይህ ተግባር ከልምምድ ባለፈ ባህል መሆኑን ክቡር ሚኒስትሩ ተናግረዋል። በማከልም ለዚህ ተግባር ድጋፍ ያደረጉ የኢትዮጵያ ውሃስራ ተቋራጮችን አመስግነዋል ። በመጨረሻም የተተከሉትን ቸችግኞች መንከባከብ ከአካባቢው ማህበረሰብ የሚጠበቅ መሆኑን ገልጸው ቀድመን ብንተክል የአካባቢ መራቆትን በመጠበቅ ለአዋሽ ወንዝ ጠቀሜታው የጎላ ይሆን ነበር ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ ዛሬ በተከልነው ልክ በረከቱ ስለሚበዛ ተንከባክበን እናጽድቅ ብለዋል። በመርሀ ግብሩ የተገኙት የአፋር ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደርና የክልሉ ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ እና ፕላን ቢሮ ሀላፊ ክቡር አሊ ሙቸሙድ የአፋር ህዝብ ከለውጡ ማግስት ችግኝ የመትከል አመለካከትን ወደ ተግባር ተቀይሮ ባህል ወደማድረግ መጥተናል ብለዋል። በክልሉ በተያዘው አመት ከ10ሚሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል አቅዶ እየሰራ መሆኑን ገልጸው ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ጋር እየተተከለ ያለው የእቅዱ አካል ነው ብለዋል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአረንጓዴ አሻራ ባለፈ ለክልሉ በጎርፍ መከላከል ፣በመጠጥ ውሃ እና በተለያዩ ተግባሮች እያገዘን በመሆኑ ሊመሠገን ይገባል ያሉት ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ አሁንም የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብ ከአካባቢው ማህበረሰብ ይጠበቃል በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። በመርሀ ግብሩ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ፣የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች የተጠሪ ተቋማት አመራሮች እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ ተሳትፈዋል።

Share this Post