በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ሀድያ ዞን የሲራሮ ባዶዋቾ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የግንባታ ቁጥጥርና ዉል አስተዳደር የማማከር አገልግሎት ስምምነት ተፈረመ፡፡

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ሀድያ ዞን የሲራሮ ባዶዋቾ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የግንባታ ቁጥጥርና ዉል አስተዳደር የማማከር አገልግሎት ስምምነት ተፈረመ፡፡ ሀምሌ 8 /2017 ዓ/ም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ሀድያ ዞን የሲራሮ ባዶዋቾ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የግንባታ ቁጥጥርና ዉል አስተዳደር የማማከር አገልግሎት ስምምነት ከለሊፍቱ አጠቃላይ የልማት ድርጅት ጋር ተፈራረመ፡፡ የግንባታ ክትትል እና ኮንትራት አስተዳደር የስምምነት ውሉን የፈረሙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ፕሮጀክቶቹ ላይ ተገቢውን ቁጥጥር እና ክትትል በማድረግ የመጠጥ ዉሃ ፕሮጀክቱ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ለዉጤት ለማብቃት እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡ የለሊፍቱ አጠቃላይ የልማት ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ አማኑኤል አሰፋ በበኩላቸው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተጣለባቸውን ሃላፊነት በብቃት በመፈጸም ስራውን ውጤታማ ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል፡፡ የሲራሮ ባዶዋቾ የመጠጥ ወሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት በብሄራዊ ዋን ዋሽ ፕሮግራም አካል በሆነው በCR-WaSH ፕሮጀክት በኩል የሚተገበር ሲሆን፤ የማማከር አገልግሎቱ ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ይደረግበታል፡፡

Share this Post