ኮንቲኒየም ሀይድሮሎጂ ሞዴሊንግ ሶፍት ዌር ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
ሀምሌ 8/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በዋቢ ሸበሌ፣ አዋሽ እና በደናክል ተፋሰሶች ላይ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር (IWRM) ለማስፈን በተቀረጸውና በጣሊያን መንግስት በሚደገፈው በባዘርኔት ፕሮጀክት በኩል ኮንቲኒየም ሀይድሮሎጂ ሞዴሊንግ ሶፍት ዌር ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
በስልጠናው የተገኙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የባዘርኔት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሞላ ረዳ ስልጠናው በሲማ ፋውንዴሽን ካምፓኒና የጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ በጋራ የተዘጋጀ የሀይድሮሎጂካል ሞዴሊንግ ስልጠና መሆኑን ገልጸው፤ ስልጠናው በዋናነት የሶፍትዌር አጠቃቀም ላይ ግንዛቤ መፍጠር፣ አጠቃላይ የሀይድሮሎጂካል ዳታ አሰባሰብንና አጠቃቀምን ለማጠናከር ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።
የውሃ አስተዳደር ዘርፍ ባለሙያችን አቅም ለመገንባት እያደረጉት ለሚገኘው አጠቃላይ ድጋፍ ሲማ ፋውንዴሽን ካምፓኒን፣ የጣሊያን የልማት ትብብር ኤጄንሲን እና የአውሮፓ ህብረትን በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና በባዚሪኔት ፕሮጀክት ስም አመስግነዋል።
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የገጸ ምድር ውሃ ዴስክ ሃላፊ አቶ ሚካኤል ብርሀኔ በበኩላቸው በሶስቱ ቤዚኖች፤ በዋቢ ሸበሌ፣ በአዋሽ እና በደናክል ላይ ተግባራዊ የሚደረግ ሞዴሊንግ መሆኑን አንስተው፤ ሞዴሊንጉ ምን እንደሚመስል ለባለሙያዎች ግንዛቤ ከመፍጠር ባሻገር ሞዴሊንጉን በ3ቱ ቤዚኖች እንዴት መጠቀም እንደሚቻል በስልጠናው የተካተተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በልጠናው ሰልጣኞች ኮንቲኒየም ሀይድሮሎጂ ሞዴሊንግ ተጠቅመው ቅድመ ማስጠንቀቂያ ፣ የውሃ ልኬት፣ የውሃ ምደባ እና ወቅታዊ ትንበያዎችን ለማዘጋጀት አቅም ይፈጥርላቸዋል ብለዋል፡፡
በስልጠናው ላይ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፣ ከኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲቲዩት፣ ከአዲስ