የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ውል ስምምነት ተደረገ፡፡

የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ውል ስምምነት ተደረገ፡፡

ሀምሌ 07/11/2017ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሶማሌ ብሔራዊ ክልል ዳሮር እና ዳኖት ወረዳዎች የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ለማከናወን ከዋሂን የቁፋሮ ድርጅት ጋር የውል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ከ427 ሚሊየን ብር ባላይ ወጪ የሚደረግበት የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ስራ በብሄራዊ የዋን ዋሽ ሮግራም የባለብዙ መንደር ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ፕሮጀክት በኩል የሚተገበር ሲሆን፤ በዳኖት ወረዳ ሶስት ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች እንዲሁም በዳሮር ወረዳ ሶስት ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች የሚቆፈሩ ይሆናል፡፡

ሰምምነቱን የተፈራረሙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ስራው ለአካባቢው አርብቶአደር ማህበረሰብ ውሃ ለማቅረብ ታሳቢ ተደርጎ ፕሮጀክቱ መቀረጹን አንስተው በ7 ወራ ውስጥ መጠናቀቅ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያቱም ከክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ጋር በመቀናጀት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

የዋሂን የቁፋሮ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ እስማኤል መዳሂን በበኩላቸው የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ስራዉን በተያዘለት የጊዜ ገደብ በጥራት አጠናቀው እንደሚያስረክቡ ቃል ገብተዋል፡፡

የማማከር ስራውን አዋሽ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ እንደሚያከናውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Share this Post