ፕሮጀክቱ ለዘመናት የቆዬ ችግራቸውን እንደሚፈታላቸው ገለጹ።

ፕሮጀክቱ ለዘመናት የቆዬ ችግራቸውን እንደሚፈታላቸው ገለጹ።

ሀምሌ 6/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ)የውሃና ኢነርጅ ሚኒስቴር በወላይታ ዞን ሻንቶ ከተማ በዋን ዋሽ ፕሮግራም ያስገነባው የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የዘመናት የቆዬ ችግሮቻቸውን እንደፈታላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የሻንቶ ከተማ ነዋሪ እና የጤና ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ምህረት ቶንታ እንደገለጹት ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የውሃ ችግር እንደነበርና አሁን ላይ የዚህ ፕሮጀክት መተግበር የመጠጥ ውሃ ፍላጎታችን ብቻ ሳይሆን ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን እንደሚፈታላቸው ገልጸዋል።

ወ/ሮ ምህረት በማከል ፕሮጀክቱ በተለይ ለሴቶች ውሃ ለመቅዳት የሚያባክኑትን ጊዜና የሚደርስባቸውን ከፍተኛ የጤና ችግር ሙሉ በሙሉ በማስቀረት ጤናማ ማህበረሰብ በመፍጠር በውሃ ብክለት የሚፈጠረውን ህመምና ሞት የሚያስቀር በመሆኑ በፕሮጀክቱ ትግበራ የተሳተፉትን አካላትን አመስግነዋል።

የከተማዋ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሆኑት ወ/ሮ እታለም ታንቶ የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ በከተማዋ በነበረው የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር ምክንያት ለአንድ ጀሪካን ውሃ እስከ 20ብር ድረስ በመክፈል ውሃ ያገኙ የነበረውን ሁኔታ አስታውሰው ችግር በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ከመሆናቸው ባሻገር ውሃ ለማስቀዳት የሚከፍሉትን ወጪም እንደሚያስቀርላቸው ገልጸዋል።

ወ/ሮ እታለም በማከል ፕሮጀክቱ ከመጠጥነት ባለፈ በከተማዋ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚሰጥና በተለይ ለትምህር ቤቶች ፣ ለጤና ተቋማት እንዲሁም ለከተማዋ እድገት ልማቱ እንዲፋጠን ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በአግባቡ ለሁሉም ህብረተሰብ መዳረስ እንዲችልና የውሃ ብክነት እንዳይፈጠር እንዲሁም በፍትሀዊነት ለመጠቀም እና ፕሮጀክቱን ለመጠበቅ የከተማው ውሃ አገልግሎት እና ህብረተሰቡ በጋራ መስራት ይጠበቅብናል በማለት አስተያየትም ሰጥተዋል።

ፕሮጀክቱ ከ208 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባና ሁለት ሪዘርቬየር ያሉት ሲሆን 29 ሺ የህብረተሰብ ክፍልን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው።

Share this Post