በበናጸማይ ወረዳ የአልተርጉድ ቀበሌ የመጠጥ ዉሃ ፕሮጀክትና በሀመር ወረዳ የዲመካ ከተማ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የግንባታ ቁጥጥርና ዉል አስተዳደር የማማከር አገልግሎት ስምምነት ተፈረመ፡፡

በበናጸማይ ወረዳ የአልተርጉድ ቀበሌ የመጠጥ ዉሃ ፕሮጀክትና በሀመር ወረዳ የዲመካ ከተማ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የግንባታ ቁጥጥርና ዉል አስተዳደር የማማከር አገልግሎት ስምምነት ተፈረመ፡፡

ሀምሌ 04 /2017 ዓ/ም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በበናጸማይ ወረዳ የአልተርጉድ ቀበሌ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክትና በሃመር ወረዳ የዲመካ ከተማ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የግንባታ ቁጥጥርና ዉል አስተዳደር የማማከር አገልግሎት ስምምነት ከደቡብ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ ጋር ተፈራረመ፡፡

የግንባታ ክትትል እና ኮንትራት አስተዳደር የስምምነት ውሉን የፈረሙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታ ማእረግ የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ሞቱማ መቃሳ ፕሮጀክቶቹ ላይ ተገቢውን ቁጥጥር እና ክትትል በማድረግ የመጠጥ ዉሃ ፕሮጀክቶቹ በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ለዉጤት ለማብቃት እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ ስራ አስኪያጅ ኢ/ር አብዲሳ ኩፎ በበኩላቸው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተጣለባቸውን ሃላፊነት በብቃት በመፈጸም ስራውን ውጤታማ ለማድረግ እንተጋለን ብለዋል፡፡

በበናጸማይ ወረዳ የአለተርጉድ ቀበሌ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክትና በሃመር ወረዳ የዲመካ ከተማ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በብሄራዊ ዋን ዋሽ ፕሮግራም አካል በሆነው በCR-WaSH ፕሮጀክት በኩል የሚተገበሩ ናቸው፡፡

Share this Post