ክቡር ሚኒስትሩ ከአለም ባንክ የስራ ሀላፊ ጋር ተወያዩ፡፡
ሀምሌ 04/2017 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚነስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብሙ ኢተፋ በአለም ባንክ የአፍሪካ ግሩፕ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዛራው ክብዌ ጋር ተወያዩ፡፡
ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደር፣ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አቅርቦትና የኢነርጂ ልማት ዘርፎች የተዋቀረ መሆኑን ጠቁመው፤ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርን ለማስፈን የሚያግዙ ተግባራት፤ የንጹህ መጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን አቅርቦትን የሚያሳልጡ ስራዎችና የሀይል ተደራሽነትን ለማስፋፋት በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል፡፡
የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን በተመለከተ ለበርካታ ዜጎች የመጠጥ ውሃ ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡
ቀጠናዊ የሀይል ትስስርን በማሳለጥ ለቀጠናው ሀገራት ሀይል ማቅረብ መቻሉንም አክለው ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር ዛራው ክበዌ በበኩላቸው በአለም ባንክ ከሰሃራ በታች የሚገኙ 22 ሀገራት ጉዳዮችን እንደሚከታተሉ አንስተው፤ ኢትዮጵያ ከሀገራቱ መካካል በአፈጻጸም ዉጤታማ መሆኗን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን የዘርፉ ባሙያዎችም በሌሎች አፍሪካ ሀገራት እያደረጉ የሚገኘው ሙያዊ አስተዋጽኦ ሊደነቅ ይገባልም ብለዋል፡፡
ባንኩ በኢትዮጵያ የሚከናወኑ ልዩ ልዩ የልማት ስራዎችን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር ዛራው ክበዌ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዲጂታል ኤግዚቢሽንንም ጎብኝተዋል፡፡