ስልጠናው ሀገራችን በውሃ ጥራት አለካክ ላይ ያለችበትን ደረጃ ያየንበት ነው ሲሉ ሰልጣኞች ገለጹ:፡
ስልጠናው ሀገራችን በውሃ ጥራት አለካክ ላይ ያለችበትን ደረጃ ያየንበት ነው ሲሉ ሰልጣኞች ገለጹ ፡፡
ሰኔ 27/2017(ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በዋቢ ሸበሌ፣ አዋሽ እና ደናክል ሃይድሮግራፊክ ተፋሰሶች ላይ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርን ለማሻሻል የሚያግዘው ስልጠና ሀገራችን በውሃ ጥራት አለካክ ላይ ያለችበትን ደረጃ ያየንበት ነው ሲሉ የስልጠናው ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢኮ ሀይድሮሎጂና ውሃ ጥራት ዴስክ ኃላፊ አቶ ይርጋለም እሱነህ ስልጠናው በዋናነት በውሃ ጥራት ላይ ያተኮረ በመሆኑ ወጥ የሆነ የአሰራር ስርዓትን በመፍጠር በዋቢ ሸበሌ፣ አዋሽ እና ደናክል ሃይድሮግራፊክ ተፋሰሶች ላይ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርን ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅዖ በማበርከት ህብረተሰቡንም ሆነ አካባቢን የሚጠቅም ዘላቂ የውሃ አጠቃቀምን ማረጋገጥ አላማ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡
እንደ ሀገር የውሃ ጥራት ክትትል ሲደረግ ሁሉም በራሱ አቀራረብ ይተገብር የነበረውን አሰራር ወጥ የሆነ አቀራረብ እንዲኖር ስልጠናው አጋዠ ነው ብለዋል።
በስልጠና ከቦታ መረጣ ጀምሮ የናሙና አወሳሰድ እና አላላክ ስርዓትን በተግባር አስደግፈን አይተናልም ብለዋል፡፡
አቶ ይርጋለም አክለውም ፕሮጀክቱ ከሚተገበርባቸው አዋሽ፣ዋቢ ሸበሌና ደናክል አካባዎች የመጡ ባለሙያዎች ሰልጥነው ሲመለሱ ተመሳሳይ የሆነ አቀራረብን እንዲተገብሩና ስራውንም በጥራ እንዲሰሩ የወሰዱት ስልጠና በእጅጉ እንደሚጠቅማቸውም ነው የገለጹት።
የትግራይ ክልል ውሃና ኢነርጂቢሮ የውሃ ጥራትና ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ ሰለሞን ገብረዮሀንስ በበኩላቸው ስልጠናው በዘርፉ አሉ ከሚባሉና በተለያዬ አቅጣጫ በበይነ መረብ ታግዞ መሰጠቱ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጸው መረጃን እንዴት ጠቃሚ ማድረግ እንደምንችል አስገንዝቦናል ብለዋል፡፡
እንደ ሀገር በስልጠናው ላይ ያየናቸው መሳሪያዎች ቢሟሉልን ሀገራችንን በውሃ ጥራት ከፍ ማድረግ እንደሚቻልም ጭምር የተገነዘብንበት ነው ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ የአማራ ክልል ውሃና ኢርጂ ቢሮ የውሃ ጥራ ባለሙያ አቶ በላቸው ይታይነህ ስልጠናው ወጥነት ያለው ጋይድላይን ለማዘጋጀት የሚረዳ ግብዓት እና ያሉብንን ክፍተቶች ሊሞላ የሚችል እውቀት ያገኘንበት ነው ብለዋል፡፡
በውሃ ጥራት፣ ቁጥጥር ተግባር ፣ በገጸ ምድር ውሃ ኬሚካላዊ እና የማይክሮባዮሎጂ ጥራት መሳሪያዎች፣ ቴክኒኮች እና ፕሮቶኮሎች ላይ ለባለሙያዎቸ ኦፕሬሽን እና ጥገና ላይ ያተኮረ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የተሰጠው ስልጠና ጥሩ ግንዛቤን ያገኘንበት ነውም ብለዋል፡፡