የአንድ ቋት ብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም የሁለተኛው ምእራፍ የመስክ ሪፖርት ግኝት ላይ ውውይት ተደረገ፡፡
ሰኔ13/2017 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአንድ ቋት ብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም የሁለተኛው ምዕራፍ የስድስት ወር ስራ አፈጻጸም የመስክ ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ቡድኑ ፕሮጀክቶቹ በሚገኙበት በሁሉም ክልሎች አንድ ወረዳና አንድ ከተማ በቦታው ተገኝተው ስራው ያለበትን ደረጃ በመገምገም በጥንካሬና በድክመት ለይተው ማቅረባቸው ሊያስመሠግናቸው ይገባል ብለዋል።
የብሔራዊ ዋን ዋሽ አስተባባሪ አቶ አብይ ግርማ ሪፖርቱን ከሚመለከታቸው ሴክተሮች የተውጣጡ 6 ቡድኖች በሁሉም ክልሎች በተመረጡ ወረዳዎችና ከተሞች በመሄድ ከፌደራል ሴክተር መስሪያ ቤቶች እና አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን መሬት ላይ ያለውን የፕሮግራሙን አፈጻጸም በጥንካሬና በድክመት በመገምገም ለየክልሉ የውሃና ሳኒቴሽን ዋሽ ስትሪንግ ኮሚቴ አባላት እና
ለቢሮ ሀላፊዎች በማቅረብ አፈጻጸምን ለማሻሻል ታሳቢ ተደርጎ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡
የመስክ ግኝቱ ለመድረኩ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ድክመቶችን በማረም ጥንካሬዎችን የምናስቀጥልበትና ቀጣዩ ፕሮግራም ምን ይመስላል ፣ ምን አይነት አፈጻጸሞች ይኖሩታል ፣ ምንስ ያካትታል የሚለውን አቅጣጫ የምናስቀምጥበትም ነው ብለዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳን ጨምሮ፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከፋይናንስ ሚኒስቴር የተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮች ፣ ባለሙያዎች እና አስተባባሪዎች ተሳትፈውበታል፡፡