በኤግዝቢሽኑ ሀገራችን ያለችበትን የእድገት ደረጃ አይተንበታል፡፡

በኤግዝቢሽኑ ሀገራችን ያለችበትን የእድገት ደረጃ አይተንበታል፡፡ ሰኔ 11/2017ዓ.ም(ው.ኢ.ሚ) በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም ለእይታ በቀረበው የውሃና ኢነርጂ ኤግዚቢሽንን እየተመለከቱ ያገኘናቸውና ነዋሪነታቸው በአሜሪካ የሆነው አቶ እውነት ላቀው ቤተሰባቸውን ይዘው ለጉብኝት የመጡ መሆናቸውን ገልጸው በጣም ዘመናዊ የሆኑ ቴክኖሎጂ ዎችን በመጠቀም የተዘጋጀው ኤግዚቢሽን ሀገራችን ያለችበትን የእድገት ደረጃ በሚገባ ያሳያል ብለዋል። አቶ እውነት በማከል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ ያለበትን ደረጃ የማየት እድል በማግኘቴ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ ብለዋል። ውሃን ከማጣራት ጋር በተያያዘ እየተሰራ ያለው ስራም ከሚኖሩበት ሀገር የሚጠቀሙት በዚህ መልኩ የተጣራ መሆኑንና ይሄ ቴክኖሎጂ በሀገሬ መጀመሩ አስደስቶኛል ብለዋል። ከሀገራችን ህዝብ ብዛት አንጻር ያለንን የውሃ ሀብት በመቆጠብ በአግባቡ ለመጠቀምና መጪው ትውልድ እንዳይቸገር ውሃን መልሶ መጠቀም አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል። በተጨማሪም በአማራጭ ኢነርጂ ላይ እየተሰራ ያለው ስራ ጥሩ መሆኑን ገለጸው ለአንድ ሀገር እድገት ወሳኙ ነገር ኢነርጂ በመሆኑ በዚሁ ዘርፍ አማራጮችን መጠቀም አስፈላጊ ነው ብለዋል። በተጨማሪም የምንጓጓለትና በትብብር የሰራነው የህዳሴ ግድባችን ያለበትን ሁኔታ በሚገርም ሁኔታ ማየታቸው እንዳስደሰታቸውና በቅርቡ ተጠናቆ የሀገራችንን ችግር እንደሚፈታ ያላቸውን ተስፋ ነግረውናል።

Share this Post