የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሙስናንና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ረገድ አርዓያ የሚሆኑ ስራዎችን መስራቱ ተገለጸ።
ሰኔ 11/2017ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) ጸረ ሙስና ኮሚሽን ያቋቋማቸው የሱፐር ቪዥን ቡድን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሙስናንና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል አርዓያ የሚሆኑ ስራዎችን መስራቱን ገልጸዋል።
ቡድኑ በሚኒስትሪው የተከናወኑ ስራዎችን ከተመለከተ በኋላ ከክቡር ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
በቆይታቸውም ሚኒስትሪው ሙስናንና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል እየሰራ ያለውን ጠንካራ ስራ፣ ከሀብት ምዝገባ፣ ከስልጠና ፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም ከፍተኛ አመራሩ ለጉዳዩ የሰጠው ትኩረት በእጅጉ የሚመሰገንና የሚያኮራ መሆኑንና በነዚህ ጠንካራ ስራዎቹም ሞዴል ተብሎ እንደተቀመጠ ለክቡር ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ስልጠናን ለባለሙያው ከመስጠትና ከአንዳንድ ክፍት መደቦች ጋር በተያያዘ ቡድኑ ላነሳቸው ጥያቄዎችም ክቡር ሚኒስትሩ ግልጽ አድርገዋል።
ከስልጠና ጋር በተያያዘ እስከ ባለሙያው ድረስ አውርዶ ለመተግበር በእቅድ እንደተያዘና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፤ የሰው ሀይል ከማሟላት አኳያም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰዎች በብቃታቸው ፣ ክፍተትን ሊሞላ በሚችል መልኩ እና እንዴት ሊሰሩ እንደሚችሉ ጭምር በመመዘን ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል።
የውሃና ኢነርጂ ውበት የሚመዘነው በውጭ በሚታየው ብቻ ሳይሆን በአገልግሎት አሰጣጣችንም በመሆኑ ማንኛውም አካል ከሰው ንከኪ ነጻ በሆነ መንገድ ቅሬታንም ሆነ አስተያየት የሚያቀርቡበት አሰራር ተዘርግቶ እየተተገበረ መሆኑንም ክቡር ሚኒስትሩ አክለው ገልጸዋል።
የሲፐር ቪዥን ቡድኑ ሰብሳቢ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ሰራ አስፈጻሚ አቶ ጌትነት ስሜ ናቸው።